የሪል እስቴት ሽያጭ ሰራተኞች የሚሰጠትን አገልግሎት በጥራትም በተድራሽነትም ከፍ ማድረግ ያለባቸው ጊዜ ላይ ድረሰናል።
የተለመዱት
“በመሃል ከተማ ….”
” በከተማችን እንብርት…”
” እኛን ሳያዩ እንዳይወስኑ…”
“በ….% ቅድመ ክፍያ…”
” በዚህ… ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ”
“ከህልሞት ጋር እናገናኞት፣ ህልሞትን ከእኛ ጋር ያሳኩ፣ እናቀማጥሎት…..” ምናምን የሚሉ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ የማይመጥኑ አማላይ መሰል ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የተለመዱ ማስታወቂያዎች በዚህ ወቅት ብቻቸውን ብዙም አዋጭ አይደሉም። ከጩኽት ብዙም አይለዩም ። ከገበያው በላይ አንገብጋቢ የሆኑ በርካታ ጉዳዮች ተከስተዋልና ትኩረት ለጉዳዮቹ ቢሰጥ መልካም ነው….
በተለይ ብዙዎች በማስታወቂያዎቻቸው ወይም ለመግዛት ከማግባባት ከሚጠቀሙባቸው አንዱ “እየወደቀ ባለው ገንዘብዎ ቤት ይግዙበት” የሚለው ይገኝበታል። እስኪ ገንዘቤን አድናለሁ ብሎ ቤት የገዛው የቀድሞ ደንበኞችሁን ዛሬ አግኙትና ቀድሞ ያጋዛችሁትን ለመሸጥ ሞክሩ…ታዩታላችሁ ። ከባድ ነው።
በዚህ ወቅት ያለውን የገንዘብ እጥረትና ገንዘብ ያለው ሰው ያለውን አማራጭና በንግድ ውስጥ ያለውን የገንዘብ አቅርቦት ፍላጎት ያላገናዘበ ከገንዘብ ነክ እውቀት እጥረት የሚመጣ ስሁት ትንተና ነው።
ሴልሶችዬ በዚህ ወቅት ገንዘብ ያለው ጌታ ነው። ብዙ ሊሰራቸው የሚችሉ በቀላሉ ያለውን ገንዘብ ሊያሳድጉለት የሚችሉ አማራጮች አሉለት። ቤት መግዛት አንድ አማራጭ እንጂ ብቸኛ አማራጭ አይደለም።
በዚህ ወቅት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ትናንሽ ጭውውት ወይም ድራማ የሚመስሉ ማስታወቂያዎች በመስራት ብቻ መጥራትና እንዲገዙ ማድረግ ትርፉ ድካም ነው። ገዢዎች ከግዙ ባሻገር በቁጥር የተቀመሩ የአዋጭነት ማሳያ ስሌቶችን ሰርተው ለማሳመን መሞከር አለባቸው።
በተጨማሪም ወደ ማስተዋወቅ ከመግባታቸው ወይም ሽያጩ ላይ ለመሳተፍ ከመወሰናቸው በፊት እነዚህን ጉዳዮች ታስቢ ቢያደጉ ጥሩ ነው
፩) የደንበኞች ወቅታዊ ፍላጎትና የመግዛት አቅም
፪) የደንበኞች ወቅታዊ ስጋቶች መገንዘብ
፫) በገበያ ውስጥ ለደንበኞች ያሏቸው ተመሳሳይ አማራጮችን አይቶ ማወዳደር
፬) ህጋዊነትና ወቅታዊ ተያያዥ ለውጦች
፭) የአልሚው ስምና ዝና
፮) ለሽያጭ የወጣው ቤት ለመሸጥ መቅለልና መክበዱ
፯) ሽያጩ የሚያስለፋውን የሚመጥን ኮሚሽን መጠየቅ
፰) በሪል እስቴት ሳይክል መሰረት ጊዜው ለገዢዎች የሚያደላ በመሆኑ የመደራደርና የማደራደር አቅምን ማዳበር
፱) ከሽያጭ ከሚጠበቅ ገቢ በተጨማሪ ቋሚ ገቢ (passive income )የሚያገኙባቸውን ስራዎች መስራት
፲) አልሚዎች በድርድር ዋጋ እንዲቀንሱ ማሳመን
ብቻ ለየት ብላችሁ በእውቀት በቅታችሁ ውጡ ካለበለዛ ለሽያጭ ያወጣችሁት ማስታወቂያ ለገበያ የወጣውን ፕሮጀክት ከማስተዋወቅ ውጪ ለእናንተ ውጤታማ አካሄድ አይሆንም። ከእናንተ በፊት የነበሩ የሽያጭ ሰራተኞችም ይህንኑ አድርገው ነው ከዘርፉ የወጡት።
እየተስተዋለ!!!
ደንበኞቻችንን እያወቅን!!!
በደሳለኝ ከበደ
ሲቪል መሀንዲስ፣ ሪል እስቴት አማካሪ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ


















