የባማኮን ሪል እስቴት ሠራተኞች “አዲስ ዓመትን በተስፋ እና በሕይወት እንቀበል!” በሚል መሪ ቃል ደም ለግሰዋል።
አንድ የደም ልገሳ ለአንድ ሰው አዲስ የሕይወት ተስፋ ሊሆን ስለሚችል፣ በመልካም ተግባር አዲሱን ዓመት መቀበል፣ ተስፋን ማብዛትና ሕይወትን መታደግ እንደሚገባ ተገልጿል።
የባማኮን ሪል እስቴት ሠራተኞች «ከግንባታ ባሻገር፣ ለሕይወት እንቆማለን» በማለት ከግንባታው ባሻገር ለበጎ ተግባር ያላቸውን ተነሳሽነት ገልፀዋል።


















