ካቮድ ኮሜርሺያል የሚያስገነባው አለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ የመኪና መሸጫ እና መለዋወጫ እቃዎች የሚሸጡበት “ካር ሞል” በመገናኛ የግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሰኔ 02/2017 ዓ.ም ተካሄደ።
“ካር ሞል” 16,300 ካሬ ላይ የሚያርፍ ሲሆን ከ6 እስከ 9 ወር ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ የካቮድ ኮሜርሻል ሴልስ ዳይሬክተር ሰብለወንጌል አያሌው ተናግራለች።
ካር ሞል በውስጡ ከ400 በላይ የተሸከርካሪ ማሳያ ቦታዎች፣ የመኪና ዲኮር ሱቆች፣ የመኪና መሰዋወጫ ሱቆች፣ ጎካርት እና የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የታክሲ እና የባስ ተርሚናል፣ 108 EV ባትሪ መሞያ ጣቢያ ( ቻርጂንግ ስቴሽን)፣ የቴክኖሎጂ ሙዚየም፣ ዘመናዊ (አውቶሜትድ ) የመኪና ማጠቢያ፣ የራይድ መኪና መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች ያካትታል ተብሏል።
ካቮድ ኮሜርሻል ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ግንባታዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሶ እነሱም ሽሮ ሜዳ የሚገኘው ጥበብ ሞል፣ ካዛንቺስ የሚገኘው ካቮድ ሞል እንዲሁም ስጦታ ሞል በአፍንጮ በር ሲሆኑ በሁሉም ፕሮጀክቶች ያለማቋረጥ ለ24 ሰዓታት እየተገነቡ በመሆኑ የካቮድ ኮሜርሺያል ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት የወደፊቷ አዲስ አበባ ዘመናዊ ገፅታ ምልክቶች አንዱ እንደሚሆኑ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡ FastMereja


















