ኮርፖሬሽኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ለሆነው የ”ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ውብና ዘመናዊ ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን አገራዊ ጥረት የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነም ነው ፡፡
በሚገነባቸው ዘመናዊ ሕንጻዎችና የመኖሪያ መንደሮች ውበትን ፣ጥራትንና እና ዘመናዊነት ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅንናቄ መሰል ድጋፎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድጓል፡፡
ምንጭ፡ የመስሪያ ቤቱ የፌስቡክ ገፅ


















