የ2025 ሚስ ወርልድ አፍሪካ አሸናፊ እና ከዓለም 2ኛ ደረጃን ያገኘችሁ ሚስ ሃሴት ደረጄ በዛሬ እለት መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል የአፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ብራንድ አምባሳደር ሆና ተሾመች።
ሃሴት ደረጄ በ2025 በተካሄደው የሚስ ወርልድ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በማግኘት የሚስ ወርልድ አፍሪካ ማዕረግን ያገኘች ሲሆን፣ ከዓለም ደግሞ 2ኛ በመሆን ሚስ ወርልድ አፍሪካ መሆኗ የሚታወስ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝናና ተሞክሮን የገኘችሁ፣ሚስ ወርልድ አፍሪካ 2025 ሃሴት ደረጄ የአፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕን የተለያዩ የሥራ ዘርፎችን፣ የካንፓኒውን ራዕይ እና ካንፓኒው የሚያከናውናቸውን የኢኮኖሚና የልማት ተግባራት ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ይጠበቃል።
የአፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ብራንድ አምባሳደር ሃሴት ደረጄ የካንፓኒውን የተለያዩ የሥራ ዘርፎችና እንደ Godo Housing and Smart Real Estete ፕሮጀክቶችን በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲታወቁ ለማድረግ፣ የካንፓኒውን ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የካንፓኒውን የእድገት ራዕይ ለማስፋት የምትሰራ መሆኑ ተገልፆዋል።
በዚሁ የብራንድ አምባሳደርነት የፊርማ ፕሮግራም ላይ ሚስ ሃሴት ደረጄ ከአፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት በመመረጤ እና የካንፓኒው ብራንድ አምባሳደር ሆኜ በመሾሜ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ተናግራለች።
ምንጭ፦ African Holding Groups


















