በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በመሸጥ ላይ የሚገኘው ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ሐይሌ ጋርመንት በግንባታ ላይ የሚገኙና በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶችን በሽያጭ ወኪልነት ለደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
የላክስአዲስ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መሀመድ ሰኢድ እንደገለጹት “በዚህ ጊዜ የማርኬቲንግ ድርጅቶች ዋና ሚና እምነትና ቃልን ወደ ተግባር የሚቀይሩ አልሚዎችን መርጦ ለደንበኞች ማቅረብ ነው።
ማርቭለስ ሪል እስቴት ደግሞ ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ነው” ብለዋል። አፓርታማዎቹ ደንበኞች በባለቤትነት ይዘው ለመኖር ወይንም አከራይተው ለመጠቀም ሲያልፍም ደግሞ ሸጠውና ለውጠው የሚያተርፉበት እድልን ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል።
የማርቭለስ ስራ አስኪያጅ አቶ ረምዚ ሀሠን በፊርማው ወቅት እንደገለጹት ድርጅታቸው በሃይሌ ጋርመንት ከዘጠኝ ፕሮጀክቶች በላይ በማልማት ላይ ያለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ሶስቱን በስኬት በማስረከብ ቀሪዎቹን በፍጥነት በመገንባት ላይ ይገኛል” ብለዋል።
በተለይም በዋና ፕሮጀክቱ ጋርመንት ሂል ከ91 ካሬ እስከ 142 ካሬ በተለያየ አማራጭ የቀረበው ባለ 21 ፎቅ መንትያ ህንፃ በፍጥነት እየተገነባ መሆኑ ተመላክቷል።
በላክስአዲስ የቀረቡ ቤቶችን በተለያየ የአከፋፈል ስርአት ከ30 ፐርሰንት ጀምሮ ቀድመው በመክፈል ቀሪውን ደግሞ የግንባታ ዕድገቱን እየተከታተሉ በሁለት ዓመት የሚከፍሉበት አማራጭ ያመቻቸ መሆኑ ተገልፁዋል።
ምንጭ:- LuxAddis Properties


















