ሜሪት ፕሮፐርቲስ የተመሰረተበትን 1ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ላለፉት ሁለት ወራት ሲያካሂድ የቆየውን ደማቅ ንቅናቄ ጥቅምት 14 ቀን በስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው የምስጋና እና የሽልማት መርሃ-ግብር በይፋ አጠናቀቀ።
ተቋሙ «አንድ ዓመት፣ አንድ ራዕይ — ቀጣዩ ምዕራፍ» በሚል መሪ ቃል ባከበረው በዚህ ታላቅ ምሽት፣ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከ60 በላይ ሰራተኞቹ በ10 የተለያዩ ዘርፎች ደማቅ እውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።
የተበረከቱት ሽልማቶችም፦
- ዘመናዊ መኪና እና የንግድ ሱቅ፣
- የኢንዶኔዢያ እና የኬንያ የጉዞ ትኬቶች፣
- አይፎን 18 ፕሮ ማክስ ስልኮች፣
- ከ50 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ የገንዘብ ስጦታዎችን ያካተቱ ነበሩ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሴልስ እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ምህረቱ ተሰማ፣ ለሜሪት ቤተሰቦች ላሳዩት ያልተቆጠበ ትጋት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ምህረቱ አክለውም «ሜሪት ፕሮፐርቲስ በዘርፉ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬት የሁላችሁም ድርሻ የላቀ ነበር፤ ተቋሙ በስራችሁ ይኮራል፣ በቀጣይም ከዚህ የላቀ ውጤታማነት እንጠብቃለን» ብለዋል።
ሜሪት ፕሮፐርቲስ ባለፉት ሁለት ወራት «የታመነ ንብረት» የሚለውን መርሁ በተግባር በማሳየት በርካታ አበይት ተግባራትን አከናውኗል።
- የኦፕን ሃውስ (Open House) መርሃ-ግብር ማካሄዱ፣
- ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ለዲቦራ ፋውንዴሽን የሙያ ስልጠና ማዕከል ግንባታ ድጋፍ ማድረጉ፣
- በመርካቶ ተክለሃይማኖት ሳይት ኤክስፖ ማካሄዱም ይታወሳል።


















