ካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን ላለፉት 20 ዓመታት በሸያጭና በገበያ ጥናት ላይ በዘርፉ በሰለጠኑና የካበተ ልምድ ባላቸውባለሙያዎች የተመሰረተና የሪል እስቴት ሻጮችን የማማከር፣ ቢሮ ማደራጀት፣ በዘርፉ የሰው ኃይል በማሰልጠን ውጤታማሥራዎች እንዲሰሩ በማስቻል በርካታ ሥራዎችን በመሥራትታዋቂና ተመራጭ ለመሆን የቻለ ድርጅት ነው፡፡
የካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን እና እህት ኩባንያው የሆነው ዶክስ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር (ዶክስ ኤቨንትስ) የሪል እስቴት ኤክስፖ በዓይነቱ ለየት ያለ ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በዚህም ኤክስፖ ላይ የተመረጡ የሪል እስቴት አልሚዎች ዋና ባለቤትና ኃላፊዎች የሚገኙበትና ለመኖሪያ ቤትና የንግድ ሱቅ ፈላጊ ሕብረተሰብ ትልቅ የንግድ ልውውጦች ኢንቨስትመንት መድረክ የሚሆን ካቦድ ሪልእስቴት ኤክስፖ 2025 “ቤት ለገዢው ሱቅ ለነጋዴው” በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 27 እስከ 29/2017 ዓ.ም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ይካሄዳል።
በዚህም ኤክስፖ ላይ በርካታ ጐብኚዎች፣ የኤክስፖ ተጠቃሚዎች፣ ተሳታፊዎችና ታላላቅ የመንግስትየሥራ ኃላፊዎች በኤክስፖ ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፡ FastMereja


















