የ2026 ጂፓወር ክሬቲቭ አዋርድስ የዓመቱ ምርጥ የይዘት ፈጣሪ አሸናፊ የ20 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የአማን ፕሮፐርቲስ አፓርታማ እንደሚሸለም ተገለጸ።
አማን ፕሮፐርቲስ ከ2026 ጂፓወር ክሬቲቭ አዋርድስ ጋር ባደረገው አጋርነት በ«ክሬይተር ኦፍ ዘ ይር» ዘርፍ ለሚያሸንፈው የዓመቱ ምርጥ የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪ 20 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ባለ ሁለት መኝታ የቅንጦት አፓርታማ ያበረክታል።
ለሽልማት የተዘጋጀው አፓርታማ በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ላፍቶ ሞል አጠገብ በሚገኘው የአማን ፕሮፐርቲስ ላፍቶ የቅንጦት አፓርታማ ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኝ ነው።

ይህ አጋርነት የፈጠራ ባለቤቶችን ለማበረታታትና ተሰጥኦአቸውን ወደ ሕይወት ለዋጭ ዕድል ለማሸጋገር ያለመ መሆኑ ታውቋል።
አማን ፕሮፐርቲስ ከአሥር ዓመታት በላይ የግንባታ ልምድ ባለው የአማኔት ቢዝነስ ግሩፕ ሥር የሚገኝ የቤት ልማት ኩባንያ ነው።
ኩባንያው እስካሁን ሦስት የአፓርታማ ሕንፃዎችንና አንድ የቪላ መንደር ፕሮጀክትን አጠናቆ ያስረከበ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአራት ሳይቶች የግንባታ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

የሽልማት መርሐ ግብሩ አዘጋጅ ቅሪንፉድ ኢቨንትስ የፈጠራ ዘርፉን ለማበረታታትና የሽልማቶቹን ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል።
ከአፓርታማው ሽልማት በተጨማሪ በእያንዳንዱ የውድድር ዘርፍ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማቶችና ከአጋር ድርጅቶች የተዘጋጁ የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚበረከቱ ተመላክቷል።
ምንጭ:- ጉርሻ page


















