አኮያ ፕሮፐርቲስ ለታላቁ የ2026 የዲሲ እና የቶሮንቶ ዲያስፖራ ኤክስፖ ዋና ስፖንሰር መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የአጋርነቱ ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ጳጉሜ 4 ቀን በአኮያ ፕሮፐርቲስ ዋና መሥሪያ ቤት የተካደ ሲሆን፣ የአኮያ ፕሮፐርቲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራ አመራሮች የኤክስፖው ብራንድ አምባሳደር ቲክቶከር ኣዶናይ ብርሃነ እንዲሁም የንብ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚድያ አካላት በተገኙበት መድረክ ላይ ነው።

በተጨማሪም፣ አኮያ ፕሮፐርቲስ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በመተባበር፣ ለቤትና ለንግድ ሱቅ ገዢዎች፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በሀገር ዉጭ ላሉ ደንበኞቹ ፣ የተራዘመ ከወለድ ነፃ የክፍያ አማራጭ አቅርቧል።
አኮያ ፕሮፐርቲስ በ14 ዓመታት የቢዝነስ ልምድ፣ በሪል እስቴት ዘርፍ ባስመዘገበው የ5 ዓመታት ስኬት እና 3 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ በማስረከብ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስተማማኝ የሪል እስቴት ዕድሎችን መፍጠሩን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ምንጭ:- Akoya Properties
















