በሲድኒ ላይ የተመሰረተው ‘ክሬስት ሮቦቲክስ ኤንድ ኧርዝ ቢዩልት’ ቴክኖሎጂ የአውስትራሊያን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እና በጨረቃ ወለል ላይ ዘላቂ መጠለያዎችን ለመገንባት ይህን ሮቦት አስተዋውቋል።
“ቻርሎት” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሮቦቱ በዓለም ላይ በዓይነቱ የመጀመሪያው ሮቦት መሆኑም ተገልጿል።
በምድር እና በጨረቃ ላይ ለመስራት የተነደፈው “ቻርሎት”፤ አነስተኛ ዋጋ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች የሚገነባ እና የወደፊቱን የጠፈር ፍለጋ የሚያሳድግ ይሆናል ነው የተባለው።
ሮቦቱ ውድ የሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማስወገድ እንደ አፈር፣ አሸዋ እና ተረፈ ምርት ያሉ የሀገር ውስጥ ጥሬ እቃዎችን ይጠቀማል።
ቴክኖሎጂው የመኖሪያ ቤቶችን እጥረት ከማቃለል እና የግንባታ ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ከተለመደው ህንፃ አሰራር እስከ 5ሺ እጥፍ ፈጣን ነው ተብሏል።
ምንጭ፡ EBC


















