አርኪ የሪል እስቴት ኤክስፖ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ከጥቅምት 14-16/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጸ።
አርኪ ሆም ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል እና በሚሊንየም አዳራሽ ባዘጋጃቸው አራት ተከታታይ ኤክስፖዎቹ ከሃያ አምስት ሺ በላይ ሰዎች የጎበኙት እንዲሁም ከስምንት መቶ ያላነሱ ሰዎች ቤት የገዙበት ትልቅ የቤት ፈላጊና የቤት አልሚዎች የሚገናኙበት ኤክስፖ ነው፡፡
የዘንድሮ ለየት የሚያደርገው ሁሉም የሪል እስቴት አልሚዎች ታላቅ ቅናሽ የሚያደርጉበት ከመሆኑ በተጨማሪም በዚህ ኤክስፖ ቤትና ሱቅ የሚገዙ የቤት እቃ በነፃ የሚሸለሙበት እድል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ለተከታታይ ሶስት አመታት አራት ትልልቅ የሪል እስቴት የቤትና ሱቅ ሽያጭ ኤክስፖዎችን ያዘጋጀና በሃገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የተዘጋጀውን ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ 2017 አዘጋጅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በጥራት እና በግንባታ ፍጥነት እንዲሁም በዲዛይናቸው በኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ የተሸለሙ ከ15 በላይ ሪል እስቴቶች የሚሳተፉበት ለ3 ተከታታይ ቀናት ማለትም ጥቅምት 14፣ 15 እና 16 በእስካይ ላይት ሆቴል በልዩ ድግስ እንዲሁም በከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ የተዘጋጀ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ሪል እስቴቶች የተለያዩ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስተዋውቁበት ልዩ መድረክ እንደሚሆንም ተገልጿል።
ምንጭ፡ FastMereja, Ethio Real Estate Award


















