ኦቪድ ሪል እስቴት (Ovid Real Estate) የ2018 የኢትዮጵያ ሚስ ወርልድ (Miss World Ethiopia 2018) እና የ2026ቱ ሚስ ወርልድ ተወዳዳሪ የሆነችውን ሩት ይርጋለምን አምባሳደሩ (Brand Ambassador) አድርጎ መሰየሙን አስታወቀ።
ተቋሙ እንደገለጸው፣ የብራንድ አምባሳደር ምርጫ ከቀላል ማስተዋወቅ ባለፈ በሦስት ዋና ዋና መሠረታዊ መስፈርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፦
እምነትና አክብሮት፦ አምባሳደሩ ለሚወክለው ተቋም እና ብራንድ እውነተኛ እምነትና አክብሮት ሊኖረው ይገባል።
የተጣጣሙ እሴቶችና ባህሪ፦ የአምባሳደሩ ስብዕና፣ እሴትና ባህሪ ከተቋሙ ማንነትና ዓላማ ጋር ሙሉ በሙሉ ሊጣጣም ይገባል።
ተስፋና ጽናትን የሚያሳይ ታሪክ፦ የሩት ይርጋለም የሕይወት ጉዞ ፈተናዎችን አልፋ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ያስጠራችበትና ለወገኗ የቆመችበት የጽናት አርአያነትን የተላበሰ ነው።
ይህ አጋርነት ኦቪድ ሪል እስቴት ለማኅበረሰብ ዕድገት፣ ለልማትና ለተሻለ መጪው ጊዜ የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያንፀባርቅ እንደሆነ ተገልጿል።
















