• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
ከኢትዮጵያ ሪል እስቴት ሽያጭ ጀርባ ያለው እውነታ

ጌቱ ከበደ (መሀንዲስ እና ንግድ አማካሪ)

ከኢትዮጵያ ሪል እስቴት ሽያጭ ጀርባ ያለው እውነታ

Betegna Team by Betegna Team
March 5, 2024
in Selling Guide
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በሚሌኒየም ግቢ ውስጥ የሪል እስቴት ኩባንያዎች ኤክስፖ ተካሂዶ ነበር። በዚያ ኤክስፖ ላይ ተገኝቼ ስለሪል እስቴት ግብይት ስልጠና ሰጥቻለሁ። በስልጠናው ላይ በርከት ያሉ የሽያጭ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ቤት ገዢዎች እና አልሚዎች ግን አላየሁም።

የሪል እስቴት አሻሻጮቹ ብዙዎቹ መሠረታዊ የግብይት ስልጠና እንኳ የላቸውም። ስለሚሸጡት ቤት እንኳ በቂ መረጃ የላቸውም። ከካሬ ሜትር ስፋት፣ ከክፍል ብዛት፣ ከዋጋ መጠን እና ከአካባቢ/ሰፈር የዘለለ መረጃ አይሰጡም። ሌላ ጥያቄ ከመጣ ቢሮ እንዲመጡ ይጋብዛሉ። የሽያጭ ኮንትራት ለማሳየት አንደቸውም አይደፍሩም። ብዙዎቹ ኮንትራቱን ዓይተውት አያውቁም።

ዲዛይን አሳይተውና አስረድተው የሚሸጡ ማግኘትማ አይታሰብም። ሁሉም “ስልክ ቁጥራችሁን ስጡን” ባዮች ናቸው። ሻጮቹ እንደ ማዕድን ፍለጋ Prospecting የሚባለው የግዢ ሂደት ቀዳሚ ደረጃን እያከናወኑ መሆኑ ነው። የአንዳንዶቹ prospecting ግን በእሳት-ወለድ አለት ነዳጅ እንደመፈለግ ነው።

ብራይት ሪል እስቴት በ2ኛው የአርኪ ሆምስ ሪል እስቴት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ

በሀገራችን ያለው የቤት ፍላጎት አሁንም ገና አልተነካም። ግን ደግሞ ለሽያጭ እየቀረቡ ያሉት የሪል እስቴት ቤቶች የአብዛኛውን ሰው የመግዛት ዓቅም ያገናዘቡ አይደሉም። ሁሉም የሚጋፉት የተወሰነ የገበያው ክፍል (niche market) ላይ ነው።

የሪል እስቴት ኩባንያ ማቋቋም እና የቡና ኤክስፖርት ንግድ ውስጥ መግባት በሀገራችን የቅርብ ጊዜ ፋሽን ሆኗል። ማንም ታዋቂ ኩባንያ እነዚህ ውስጥ ያልገባ የለም። ጥቂት ጠርቀም ያለ ብር ካለ ሪል እስቴት ውስጥ መግባት ማንም መንገደኛ የሚመክረው (no brainier) ምክር ሆኗል።

የሪል እስቴት ቤት ሽያጭ ውድድሩ ጦፏል። የአፓርታማ ሽያጭ ውትወታ አትክልት ተራ ውስጥ ፌስታል ከሚሸጡ አስቸጋሪ ልጆች እና በየአደባባዩ የባንክ አካውንት ክፈቱ ከሚሉት ወትዋቾች ጋር ተመሳሳይ ሆኗል። በተመሳሳይ ስልት ሁሉም ይጋፋል፣ ያስቸግራል።

ለሽያጭ ሠራተኞቹ አዝናለሁ። እንዲያም ሆኖ አንድ ቤት ሲሸጡ ጠቀም ያለ ኮሚሽን ስለሚያገኙ ብዙዎች ሥራውን እንደሚወዱት ይናገራሉ። ያልተማረ፣ የተማረ፣ ህክምና፣ ምህንድስና፣ ማኔጅመንት ያጠና፣ ቆንጆ መልክና ሳቢ ቁመና ያለው መናገር ብቻ ሳይሆን አሳምሮ መወትወት የቻለው ሁሉ የሚገባበት መስክ ሆኗል የሪል እስቴት ሽያጭ ሥራ።

የ2ኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ ተሳታፊዎች

የሪል እስቴት ኩባንያዎቹ አንዱ ከሌላው በምን እንደሚለዩ አያውቁም። ለሽያጭ የሚናገሩት ማስታወቂያም ተመሳሳይ ነው። ዒላማ ያደረጉትም በውጭ ሀገር የሚኖሩትን ዳያስፖራዎች ነው። አሻሻጮችም “ባትኖርበትም ለኢንቨስትመንት ይሆናል” ይላሉ። “እንዴት?” ለሚለው ጥያቄ ግን አጥጋቢ መልስ የላቸውም። አብዛኛው የሪል እስቴት ኩባንያ ተመሳሳይ የቢዝነስ ሞዴል የሚጠቀም ነው።

ኩባንያዎቹ አንዳቸው ከሌላው የሚወዳደሩት ግን በምንድን ነው?
እጅግ በጣም የሚበዙት ኩባንያዎች የሚወዳደሩት በዋጋ ቢሆንም፣ ዋጋው ሊቀንስ የሚገባው የአፓርታማ ዋጋ ዛሬም ዋጋው ላይ እንደተሰቀለ ነው። አብዛኞቹ ሻጮች የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ እንደሚችል አያውቁም። ይህንን ማወቅ የእነርሱም ሥራ አይደለም፣ ቢያውቁም ምንም ሊያደርጉት አይችሉም። ቤቱ የሚሠራበት ቦታ እና ዲዛይን አንዴ ተወስኗል።

ብዙዎቹ የሪል እስቴት አልሚዎች በምን ተወዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚችሉም አያውቁም። ሁሉም ተነስቶ የፈረደበትን Location እና የካሬ ሜትር ዋጋ እየጠራ ለመወዳደር ይሞክራል። “መሃል አዲሳባ ላይ የሚገኝ” በማለት ቤት ለመሸጥ ማስተዋወቅ ዋና ጉዳይ ሆኗል። ከመሃል ፒያሳ እና ስቴድየም ይልቅ ውድ ቤቶች የት እንዳሉ ሻጮች የተረዱ አይመስሉም። አንዱ ሰፈር ከሌላው በምን እንደሚለይ የተገነዘቡም አይመስልም። ለአብዛኛው ቤት ገዢ ቦሌ፣ ሜክሲኮ፣ መስቀል ፍላወር፣ አራት ኪሎ፣ 22፣ ገርጂ ባሉ ቤቶች መካከል ይህ ነው የሚባል የLocation ልዩነት የለም። ለከተማው ማዕከል ለፒያሳ ቅርብ መሆንን ዋጋ የሚሰጡትም አልጠፉም። እንዲያ ከሆነ ከሰሚት ይልቅ ለፒያሳ ቅርብ የሆኑት አስኮ፣ ሩፋኤል እና ፈረንሳይ ለምን በሪል እስቴት ኩባንያዎች እንዳልታዩ መልስ የለም።

የሪል እስቴት ቤት ዋጋ አሁንም ዋና የመወዳደሪያ ጉዳይ ነው። የቤት ዋጋ የናረው በዋነኛነት በብረትና በስሚንቶ ዋጋ መናር ምክንያት ብቻ አይደለም። የቤት ዋጋ ንረት ዋና ምክንያት የመሬት የሊዝ ዋጋ ከፍተኛነት ነው። ይህንን ማርክስ የሚቻለው ደግሞ በሰፈር ምርጫ፣ በVolume ብዛት እና በዲዛይን ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ እይታ ከአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት

የሪል እስቴት ገበያው ሌላ ዋና ችግሮችም አሉበት። አሁንም የታማኝነት ችግር የሪል እስቴት ገበያው ዋና ችግር ነው። የፕሮጀክት ማኔጅመንት ችግር እና የካፒታል ዓቅም ማነስ ለታማኝነት ችግር እና ቤት በጊዜ አለማስረከብ ዋና ችግር ነው። የዚህ ችግር ምንጭ ደግሞ የተድበሰበሰ ኮንትራት ነው። እስካሁን ግልጽ ያለ ኮንትራት የሚያሳይ የሪል እስቴት ኩባንያ አልገጠመኝም። በዚህ ዘመን በላውንደሪ እጥበት ቤት ኮንትራት ዓይነት ቤት ለመሸጥ መሞከር እድሜው አጭር ነው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የቤት አሻሻጭ ብቻ ሳይሆን ቤት አጋዦችም ይፈጠራሉ። ያኔ ኮንትራት ውስጥ ያለች ስንቅር ያለች ቃል ሁሉ ትበጠራለች። ያኔ የኮንትራት ግልጽነት ዋና መወዳደሪያ መሆኑ አይቀርም።

ያኔ የፕሮጀክት ማኔጅመንትና የማስረከቢያ ጊዜ ፍጥነት፣ ታማኝነት ዋና መወዳደሪያ ይሆናሉ። ያኔ የግንባታ ከፍታና የፎቅ ወለል ብዛትም ይቀየራል። ያኔ የቤት ዋጋም በብዙዎች የሚደፈር ይሆናል። እስከዚያው ግን ብዙዎች
"ፊርማና ወረቀት ጠፊ ነው ተቀዳጅ
መተማመን ብቻ ይበቃል ለወዳጅ"

እያሉ ሳያጣሩ ቸኩለው ለቤት ቅድመ-ክፍያ ከፍለው “ሙዝ አለኝ በሰማይ፣ ልጣጩንም አላይ” እያሉ መክረማቸው የማይቀር ነው። ለኢንቨስትመንት ብለው ከባንክ ተበድረው የገዙትም የኪራይ እና የመሸጫ ዋጋው ሲቀንስ ምን እንደሚሆኑ ፈጣሪ ይወቅ።

የሪል እስቴት ግብይት ያለ መካሪ እና አጋዥ ዘው ተብሎ የሚገባበት ዘመን መሆኑ እያበቃ ነው። Real Estate is no more a no brainier market. አንዳንዶች ችግር ውስጥ እየገቡ ነው። ቆም ብለህ አስበህ፣ ጥሩ ቢዝነስ ሞዴል ይዘህ ልትሠራ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነህ። ያኔ ሻጮችህ እንደ አትክልት ተራ ፌስታል ሻጭ በውትወታ አይሸጡም። ገዢህ ወዳንተ ተስቦ ይመጣል።

ገዢህን ምን ይስበዋል?

አበባ ንብን እንደሚስብ ጥሩ የቢዝነስ ሞዴልም ገዥን ይስባል። ለሪል እስቴትህም፣ ለቡና ኤክስፖርትህም፣ ለየትኛውም ቢዝነስህ ኧረ ለሰላማዊ ኑሮም ጥሩ ሞዴል ይኑርህ። ለመሆኑ የቢዝነስ ሞዴልህ ምን ይመስላል? ሞዴል ከሌለህ ፈትሸህ አስፈትሸህ ጥሩ የቢዝነስ ሞዴል ያዝ።

ምንጭ፡ ጌቱ ከበደ (መሀንዲስ እና ንግድ አማካሪ)

Tags: Editors PickEngineer Getu kebede
Previous Post

አንድ ቢልዮን ብር ቀብድ የተከፈለበት ህንፃ ሽያጭ መቋረጡን ቢጂአይ ኢትዮጵያ አስታወቀ

Next Post

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች የመቶኛ ቁጥሮች
Selling Guide

የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች የመቶኛ ቁጥሮች

November 18, 2025
ብዙ ያልተባለለት የሪል እስቴት የሽያጭ ባለሙያዎች ልፋት
Selling Guide

ብዙ ያልተባለለት የሪል እስቴት የሽያጭ ባለሙያዎች ልፋት

December 4, 2024
ሴልሶችዬ ደንበኞቻችንን እንወቃቸው
Selling Guide

ሴልሶችዬ ደንበኞቻችንን እንወቃቸው

November 9, 2024
Next Post
ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
ቴምር ሪል እስቴት ለደራሲና ዳይሬክተር ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የቤት ስጦታ አበረከተለት

ቴምር ሪል እስቴት ለደራሲና ዳይሬክተር ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የቤት ስጦታ አበረከተለት

March 18, 2026
አልሚዎች በተገደበ የጊዜ ሰሌዳ የተላለፉ ቦታዎችን አልምተው ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አልሚዎች በተገደበ የጊዜ ሰሌዳ የተላለፉ ቦታዎችን አልምተው ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

March 18, 2026
በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዲያስፖራ ባለሀብቶች የሪል እስቴት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለጸ

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዲያስፖራ ባለሀብቶች የሪል እስቴት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለጸ

March 17, 2026
ከተማ አስተዳደሩ 315 የንግድ ሱቆችን ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፈ

ከተማ አስተዳደሩ 315 የንግድ ሱቆችን ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፈ

March 17, 2026
የጊፍት ሪል እስቴት ባለቤት አንድ ሱቅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር ለመቄዶንያ

የጊፍት ሪል እስቴት ባለቤት አንድ ሱቅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር ለመቄዶንያ

March 16, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (20)
  • Construction & Projects (25)
  • Construction Material Supply (6)
  • Design & Innovation (12)
    • Architecture (1)
    • Technology (10)
  • Global (1)
  • Government Housing (47)
  • Insights & Profiles (12)
  • Legal Updates (75)
    • Community Complaints (5)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (10)
  • Property Handover (9)
  • Real Estate Guides (11)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (6)
  • Sales & Marketing (35)
  • Tenders & Bids (54)
    • Land Lease (27)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2024 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent