ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን” በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል። ” ሲል አሳውቋል።
“ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል” ብሏል።

ቀደም ብሎ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሜክሲኮ የሚገኘውንና የቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ሥፍራ ለመግዛት መስማማታቸውን ከሁለቱም ወገን መገለጹ ይታወሳል። ለዚህም ክድመ ክፍያ አንድ ቢልዮን ብር መክፈሉን ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቁ መፍልፁ የሚታወስ ነው።
ምንጭ፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ

















