ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ፣ በተመረጡ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቦሌ አትላስ የሾሪንግ ስራ መጨረሱን እና ለሽያጭ ክፍት መደረጉን እንዲሁም ካዛንቺስ ላይ የግንባታ ሥራውን አምስት ቤዝመንት ጨርሶ ግራውንድ ወለል ላይ በደረሰው ሳይት በይፋ ለሽያጭ ክፍት ማድረጉን ገለጸ።
ድርጅቱ አዲሱን ምዕራፍ ምክንያት በማድረግ፣ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዥዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ባቀረበው መረጃ መሰረት፣ ከ55 ካሬ ሜትር ስቱዲዮ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ 165 ካሬ ሜትር ሰፊ የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የንግድ ሱቆች በሽያጭ ላይ ይገኛሉ ብሏል።
የመኖሪያና የንግድ ቦታዎቹ ዋጋ በካሬ ሜትር ከብር 80,500 ጀምሮ የተመደበ ሲሆን፣ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የዋጋ ቅናሽ እሰከ መሰከረም 30 -2019 ዓ.ም ብቻ የሚቆይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ እንዲሁም ከዛሬ ነሐሴ 20 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአትላስ
ሳይት ላይ የሽያጭ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።
በተጨማሪም የገበያ የምንዛሬ ጭማሪም ሆነ የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መለዋወጥ ሳይጋረጡ፣ ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውንተ አጠናቀው በጊዜው የሚረከቡበት የዋጋ ዋስትና መመቻቸቱም ተገልጿል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እና ለሁለት ት/ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
ምንጭ:- Arts Tv World
















