• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
የሲሲዲ ዴቨሎፐርስ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

የሲሲዲ ዴቨሎፐርስ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

Betegna Team by Betegna Team
August 15, 2025
in Legal Updates
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በሸገር ከተማ አስተዳዳር በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ በርካታ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን (መንደሮችን) በመገንባትና ‹‹ሲሲዲ›› በመባል የሚታወቀው ‹‹ካንትሪ ክለብ ዴቨሎፐርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እኩል ባለድርሻ (50 በመቶ) እና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት መሰለ ኃይሌ ብሩ (ዶ/ር)፣ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በደረሰ የፍትሐ ብሔር ክስ ክርክር ተረትተው፣ ከሥራ አስኪያጅነት ኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

መሰለ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ምክንያት የሆነው የፍትሐ ብሔር ክስ የተመሠረተባቸው፣ የሲሲዲ ማኅበር እኩል ባለድርሻ (50 በመቶ) በሆኑት አቶ ቶክቻ ዓለማየሁ ከተማ (ኢንጂነር) ነው፡፡

አቶ ቶክቻ (ኢንጂነር) በመሰለ (ዶ/ር) ላይ ክስ የመሠረቱት በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የነበረ ሲሆን፣ የክሱ መነሻ ምክንያትም፣ ካንትሪ ክለብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መሰለ (ዶ/ር)፣ የማኅበሩን የሒሳብ ሪፖርት አዛብቶ በማቅረብ፣ የማኅበሩን ደንበኞችና ከሳሽን (አቶ ቶክቻን) መብት የሚጎዳ ድርጊት በመፈጸማቸው የማኅበሩ ሥራ አደጋ ላይ መውደቁን፣ በማኅበሩ ያልተመዘገቡ ንብረቶች አያያዝ ለምዝበራ የተመቻቹ እንዲሆኑ በማድረግ፣ 860 የማኅበሩ ደንበኞች ሙሉ በሙሉ ክፍያ የፈጸሙ ቢሆንም፣ የቤት ግንባታው እንዲዘገይ በማድረግና ማኅበሩ በፈጸመው ውል መሠረት ግንባታ ስላልተፈጸመ ደንበኞች ጥያቄ ቢያቀርቡ ማኅበሩ ለውድቀት የሚዳረግ በመሆኑና ማኅበሩ በከፈታቸው 24 የባንክ ሒሳቦች ያለውን የሒሳብ ሚዛን ለማወቅ አዳጋች መሆኑ እንደሆነ በክሱ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ ወይም በሁለቱም ባለድርሻዎች መካከል ብርቱ የሆነ አለመግባባት ስላለ፣ በማኅበሩ ውሳኔና ድምፅ አሰጣጥ ሒደት ላይ ዕልባት መስጠት ስለማይቻል፣ በማኅበሩ አባላት ላይም ሆነ በሦስተኛ ወገን ገንዘብ ጠያቂዎች ላይ የማይካስና የማይተካ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ፣ ማኅበሩ እንዲፈርስ ወይም መሰለ (ዶ/ር) ድርሻቸውን ይዘው ከማኅበሩ እንዲወጡ፣ ከሳሽ አቶ ቶክቻው ዳኝነት ጠይቀው እንደነበር የፍርድ ሰነዱ ያብራራል፡፡

ለቀረበባቸው የፍትሐ ብሔር ክስ ለሥር ፍርድ ቤት (የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት) መልስ የሰጡት መሰለ (ዶ/ር)፣ ከሳሽ ለፍርድ ቤት ላቀረቡት ክስ ምክንያት ያደጉት ከላይ የተጠቀሱት የክስ ምክንያቶች ሕጋዊ ውጤትና ተቀባይነት የሌላቸው፣ ሰነዶችን በማዛባት የቀረቡ መሆናቸውንና እሳቸው ማኅበሩ የተቋቋመበትን ዓላማ ተከትለው እየሠሩ መሆኑን በመጥቀስ ከሥራ አስኪያጅነት ሊነሱ እንደማይገባ ተከራክረዋል፡፡

የማኅበሩን ዓላማ ማሳካት አልተቻለም ቢባል እንኳን፣ የተወሰኑ አባላት ድርሻቸውን ይዘው እንዲወጡ ተደርጎ ቀሪዎቹን ማስቀጠል የሚቻል በመሆኑ፣ ማኅበሩ መፍረስ እንደሌለበት በመግለጽ መሰለ (ዶ/ር) ተከራክረዋል፡፡

ከሳሽ (አቶ ቶክቻ) ማኅበሩን ጠቅልለው ለመያዝ መጠየቃቸው ተገቢ አለመሆኑንና እንዲያውም ከሳሽ (አቶ ቶክቻው) ድርሻቸውን ወስደው ከማኅበሩ እንዲወጡ ሲሉ መሰለ (ዶ/ር) በመልሳቸው ጠይቀዋል፡፡

የሁለቱን ባለድርሻዎች ክርክር የሰማው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ተከሳሽ መሰለ (ዶ/ር) የከሳሽ (አቶ ቶክቻ) የመሠረቱባቸውን ክስ በመቃወም ማለትም፣ በሁለቱ ባለድርሻዎች መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ አለመኖሩን፣ ድርጅቱ ሊፈርስ እንደማይገባና መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ የሚያደርግ የቀረበው የኦዲት ሪፖርት በገለልተኛ የሒሳብ ባለሙያ ኦዲት ሳይደረግና የባከነ ንብረት መኖሩ ሳይታወቅ፣ ከሥራ አስኪያጅነት ሊነሱ እንደማይገባ በመፍረድ ክሱን ውድቅ አድርጎ መዝገቡን ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ዘግቶት እንደነበር የጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ሰነድ ያስረዳል፡፡

በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ውሳኔ ቅር የተሰኙት ከሳሽ (አቶ ቶክቻ) ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ቅሬታና የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን መዝገብ አስቀርቦ በይግባኙ ላይ ካከራከረ በኋላ፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ፣ ማኅበሩ ሊፈርስ አይገባም ማለቱ ተገቢ መሆኑን በማፅደቅ፣ ነገር ግን ሁለቱም ባለድርሻዎች እኩል የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው በመሆኑና በመካከላቸው አለመተማመንና አለመግባባት ከተፈጠረ በንግድ ሕግ ቁጥር 527(3) ድንጋጌ መሠረት መሰለን (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት ለማንሳት በቂ ምክንያት እንደሚሆን፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በፍርዱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በማኅበሩ በተፈጠረው አለመግባባትና አለመተማመን ምክንያት ማኅበሩ ከሚፈርስ ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነታቸው ማንሳት ተገቢ መሆኑን በመግለጽ፣ መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ ሲል ኅዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱንም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ያሳያል፡፡

ተከሳሽ መሰለ (ዶ/ር) በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ታኅሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ፍትሐ ብሔር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል፡፡ መሰለ (ዶ/ር) ባቀረቡት ይግባኝ የማኅበሩ ሒሳብና አስተዳደር በገለልተኛ ኦዲተር መግለጫ ቀርቦ ‹‹ከሥራ አስኪያጅነት ሊነሱ ይገባል? ወይስ አይገባም?›› በሚለው ጭብጥ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ፣ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341 ድንጋጌ መሠረት ጉዳዩን ለሥር ፍርድ ቤት መመለስ እንጂ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት ወጥቶ ከሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ መወሰኑ ተገቢም የሕግ አግባብም አለመሆኑን አስረድተው፣ በንግድ ሕግ ቁጥር 515(2) እና በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ (9) መሠረት፣ ማኅበሩን የማስተዳደር ሥልጣን የሥራ አስኪያጅ በመሆኑና የአስተዳደር ጉዳዮችን ከከሳሽ (ቶክቻ) ጋር እየተመካከረ የሚወስንበት የሕግ አግባብ የሌለ መሆኑን በመጥቀስ፣ የተሰጠው ውሳኔ አግባብ አለመሆኑን ተከራክረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤት የድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሚሾምበት የሕግ አግባብ ስለሌለ፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ ‹‹ተከሳሽ (መሰለ (ዶ/ር)) ከሥራ አስኪያጅነት ሊነሱ አይገባም›› ብሎ እንዲወስንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ‹‹ይግባኝ ባይ መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት ሊነሱ ይገባል? ወይስ አይገባል?›› የሚለውን ጭብጥ በመያዝ፣ መልስ ሰጪ (አቶ ቶክቻ) ይግባኝ ባይ መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ የጠየቁበትን ምክንያት የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ያቀረቡት መልስ በመስማት መዝገቡን መርምሯል፡፡

ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ቶክቻና መሰለ (ዶ/ር) በማኅበሩ ውስጥ እኩል ድርሻ ያላቸው ሆነው፣ ይግባኝ ባይ (መሰለ (ዶ/ር)) የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ በመካከላቸው አለመተማመን ተፈጥሯል፡፡ አለመተማመን በተፈጠረበት ሁኔታ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መቀጠል፣ ተስማምቶ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ስለማያስችል፣ ደግሞም ሁለቱም አለመስማማት ላይ መድረሳቸውን ያልካዱ በመሆናቸው፣ በንግድ ሕግ ቁጥር 517 (3) ድንጋጌ መሠረት፣ ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነት ለማንሳት በቂ ምክንያት መሆኑን ደንግጎ ስለሚገኝ፣ ይግባኝ ባይ መሰለ (ዶ/ር) ከሥራ አስኪያጅነት መነሳቸው የሚነቀፍ አለመሆኑንና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔን ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በማጽደቅ፣ መሰለ (ዶ/ር) ከካንትሪ ክለብ ዴቨሎፐርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅነታቸው በንግድ ሕግ ቁጥር 515፣ 516 እና 517(3) ድንጋጌዎች መሠረት መነሳታቸው አግባብ መሆኑን በማጽናት ፍርድ ሰጥቷል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ኅዳር 9 ቀን 2017 የሰጠውን ውሳኔ፣ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) ድንጋጌ መሠረት በማጽናት ፍርድ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፡ Ethiopian Reporter

Tags: CCD Developerscrime and justiceEthiopia real estatelegal updatesreal estate justiceSupreme Court Ethiopia
Previous Post

በአዲስ አበባ ብቻ 141 ሰዎች በሕንፃ ግንባታ ሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ

Next Post

የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ
Legal Updates

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
የመሬት ይዞታ ደንብ ማሻሻያ እና የልማት ፕሮጀክቶች መሬት ምደባ ጸደቁ
Legal Updates

የመሬት ይዞታ ደንብ ማሻሻያ እና የልማት ፕሮጀክቶች መሬት ምደባ ጸደቁ

October 27, 2026
በ2015 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ በገባ ይዞታ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት አዲስ የአሰራር ስርዓት ተዘረጋ
Legal Updates

በ2015 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ በገባ ይዞታ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት አዲስ የአሰራር ስርዓት ተዘረጋ

September 28, 2026
Next Post
የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ

የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent