የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ መራዘሙን ስለማሳወቅ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ እና የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማስተላለፍ ከመስከረም 22 ቀን 2018 ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና የተጫራቾችን ፍላጎት መነሻ በማድረግ እና ለዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ግዥ በቂ ጊዜ ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መግዣ እና መመለሻ ጊዜን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም የጨረታ ሰነድ የመግዣ እና የመወዳደሪያ ሃሳብ የመመለሻ ጊዜ ከጥቅምት 06 ቀን 2018 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ድረስ ላሉት 11 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) የተራዘመ ሲሆን
ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2018 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በጨረታ መመሪያው ክፍል አንድ አንቀጽ 17 በተገለፀው ቅደም ተከተል መሰረት የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን፤
የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በኦንላይን (https://addishousebid.gov.et/) ሲስተም ወይም በአካል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 1፡ዐዐ ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ



















