የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ከነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከጨረታ ተሳታፊዎች ፍላጎት በመነሳት እና ለዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መመለሻ በቂ ጊዜ ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መሸጫና መመለሻ ጊዜን ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ በኮርፖሬሽኑ ስለታመነበት ከመስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር/10 ተከታታይ የሥራ ቀናት/ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ/ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በጨረታ መመሪያው በተገለጸው ቅደም ተከተል መሠረት ከጥቅምት 08 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡



















