• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

Betegna Team by Betegna Team
November 21, 2026
in Community Complaints
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ምድብ ችሎት በፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ (በአሁኑ ስያሜው ፍሊንትስቶንስ አ.ማ) ባለቤትነት ስር የሚገኙ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ (የፍርድ ባለመብቶች) የተወሰነላቸው የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ትዕዛዝ ሰጠ።

ችሎቱ ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ በ87 የፍርድ ባለመብቶች እና በፍርድ ባለዕዳው ፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ መካከል የነበረውን የፍርድ አፈጻጸም ክርክር መርምሮ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የፌዴራል ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በቀድሞው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 (በአሁኑ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ) “ቦሌ በሻሌ” በሚባለው ስፍራ፣ በካርታ ቁጥር ቦሌ10/69/1/6/43191/00 በሆነው ይዞታ ላይ በፍሊንትስቶንስ ስም ተመዝግበው የሚገኙ አፓርትመንቶችን በመለየት በሐራጅ እንዲሸጡ ታዟል።

በሐራጅ የሚሸጡት ቤቶች የፍርድ ባለዕዳው የተወሰነበትን ዕዳ ለመሸፈን የሚችሉ 80 በመቶ እና ከዚያ በላይ የግንባታ ደረጃ ላይ የደረሱ እንዲሆኑ ችሎቱ አዟል።

ሆኖም እነዚህ ቤቶች ዕዳውን ለመሸፈን በቂ ካልሆኑ ወይም በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቤቶች ከሌሉ፣ ከ80 በመቶ በታች የግንባታ ደረጃ ላይ ያሉትን ቤቶችም ቢሆን በሐራጅ በመሸጥ ለባለመብቶች የተወሰነላቸው ገንዘብ እንዲከፈልና ተራፊ ገንዘብ ካለ ለድርጅቱ እንዲመለስ ተወስኗል።

ይህ ረዘም ላለ ጊዜ የቆየው የሕግ ክርክር የተጀመረው ፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ (በአሁኑ ስያሜው ፍሊንትስቶንስ አ.ማ) ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ “ቦሌ በሻሌ” በተባለ ስፍራ የጋራ መኖሪያ ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከደንበኞቹ ጋር የገባውን ውል ማክበር ባለመቻሉ ነው።

በውሉ መሠረት ድርጅቱ ግዥ ከተፈጸመበት ዓመት ጀምሮ በሚታሰብ 28+2 ወራት ውስጥ ቤቶቹን ገንብቶ ማስረከብ ቢኖርበትም፣ ግንባታውን በተደጋጋሚ በማጓተቱ ደንበኞቹ ለዓመታት ርክክብ ሳያገኙ ቆይተዋል።

ይህንን ተከትሎ 212 የቤት ገዢዎች በጋራ በመሆን ጉዳዩን ወደ ግልግል ዳኝነት ጉባኤ ወስደው ክስ የመሠረቱ ሲሆን፣ ጉባኤውም ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ዝርዝር ብይን ሰጥቶ ነበር።

በዚህ ብይን መሠረት ድርጅቱ ለመዘግየቱ ያቀረባቸውን እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የሰሜኑ ጦርነት፣ የብር የመግዛት አቅም መቀነስና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያሉ ምክንያቶችን ጉባኤው ውድቅ በማድረግ፣ በአማካይ የካሬ ሜትር ዋጋ 13,700 ብር ስሌት መሠረት ለ212ቱም ከሳሾች በድምሩ ከ282 ሚሊየን 780 ሺህ ብር በላይ ካሳ ከወለድና ተያያዥ ወጪዎች ጋር እንዲከፈላቸው ወስኗል።

ከእነዚህ ከሳሾች መካከል በግልግል ጉባኤው ውሳኔ ያልተስማሙ 103 ደንበኞች፣ የካሳ ስሌቱ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ (በካሬ ሜትር 99,000 ብር) ታስቦ እንዲከፈላቸው በመጠየቅ ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መውሰዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ፍሊንትስቶንስ በበኩሉ ቤቶቹን አጠናቆ ለማስረከብ በውል ማሻሻያ በካሬ ሜትር 24,500 ብር ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረበውን አማራጭ ከሳሾቹ ባለመቀበላቸው፣ ጉዳታቸው ሊሰላ የሚገባው በዚሁ 24,500 ብር ልዩነት መሆን እንዳለበት ሲከራከር ቆይቷል።

በመጨረሻም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የከሳሾችን የ99,000 ብር የገበያ ዋጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፣ የግልግል ዳኝነት ጉባኤውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቷል።

በዚህም መሠረት ድርጅቱ ቤቶቹን ባለማስረከቡ ምክንያት ለ103ቱ ከሳሾች የከፈሉትን ዋና ገንዘብ ከወለድ ጋር እንዲመልስና በአጠቃላይ 224 ሚሊየን 430 ሺህ ብር የካሳ ክፍያ እንዲፈጽም መወሰኑ ይታወሳል።

የአሁኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝም በግልግል ዳኝነት ጉባኤው በሰኔ 01/2016 ዓ.ም የተሰጠው ፍርድና ውሳኔ በተግባር እንዲፈጸም የመጨረሻውን የአፈጻጸም መንገድ የከፈተ ሲሆን፣ መዝገቡም ያልተፈጸመ ነገር ካለ የሚንቀሳቀስ ሆኖ ለጊዜው የተዘጋ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከብያኔ ሰነዱ ላይ ተረድቷል።

ምንጭ:- ቲክቫህ ኢትዮጵያ

Tags: Flintstonehomesፍሊንትስቶን ሆምስ
Previous Post

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

Next Post

ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

በኖህ ሪል እስቴት እና በቤት ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት አመራ
Community Complaints

በኖህ ሪል እስቴት እና በቤት ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት አመራ

July 21, 2026
ፍሊንትስቶንስ ለደንበኞቹ ከ282 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነ
Community Complaints

ፍሊንትስቶንስ ለደንበኞቹ ከ282 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነ

July 18, 2026
ኖህ ሪል እስቴት በቤት ገዥ ደንበኞቹ ቅሬታ ቀረበበት
Community Complaints

ኖህ ሪል እስቴት በቤት ገዥ ደንበኞቹ ቅሬታ ቀረበበት

May 28, 2026
Next Post
ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
ቴምር ሪል እስቴት ሦስት አዳዲስ የግንባታ ሳይቶችን አስተዋወቀ

ቴምር ሪል እስቴት ሦስት አዳዲስ የግንባታ ሳይቶችን አስተዋወቀ

November 22, 2026
በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

November 22, 2026
ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

November 22, 2026
የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

November 21, 2026
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (21)
  • Legal Updates (90)
    • Community Complaints (9)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (17)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (14)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (68)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent