• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

Betegna Team by Betegna Team
November 22, 2026
in Property Handover
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ሁዳ ፕሮፐርቲስ (Huda Properties) ለደንበኞቹ ከገባው ቃል ቀደም ብሎ አደይ አበባ ስቴድየም አካባቢ (በተለምዶ 24 ቀበሌ) የገነባቸውን ቤቶች በልዩ ሥነ -ሥርዓት ለባለቤቶቹ አስረከበ።

ቅዳሜ ህዳር 12/2019 ዓ.ም በሳይቱ ላይ በተደረገው የቤቶች ቁልፍ ርክክብ ሥርዓቱ የተለያዩ እንግዶችና የድርጅቱ አመራሮች እንደታደሙ ለማወቅ ተችሏል።

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኢንጂነር መስፍን ነገዎ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ጀበል ጀማል፤ የሁዳ መሥራችና ባለቤት ኢንጂነር ኡመር ያሲን በመርሀ ግብሩ ላይ ታድመዋል።

ቤቶቹን የተረከቡ ደንበኞች እንዳሉት ድርጅቱ አስረክባለው ካለበት ቀን ቀደም ብሎ ቤቱን ለማስረከብ በመቻሉ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የመኖሪያ ቤቶቹ ባለ አንድ፣ ባለ ሁለት እና ባለ ሦስት መኝታ አማራጮችን ያካተቱ ናቸው።

ሁዳ አደይ ሳይት

ባለአንድ መኝታ ቤቶቹ 90 ካሬ ሜትር፣ ባለሁለት መኝታዎቹ 105 እና 110 ካሬ ሜትር፣ ባለሦስት መኝታዎቹ ደግሞ 140 እና 145 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሁለት አማራጮችን መያዛቸውን የሁዳ ፕሮፐርቲስ ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ምስጋናው በለጠ ተናግረዋል።

ሕንጻው የከርሰምድር ውሃ የወጣለት ብሎም ትራንስፎርመር እና ጀነሬተር ያለው መኾኑንም ተናግረዋል።

በ2009 ዓ.ም የተመሠረተው ሁዳ ኢንጂነሪንግ ወደ ሪል እስቴት ዘርፍ የገባው በ2015 ዓ.ም ነው።

በወቅቱ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና አቅርቦትን በተመለከተ ባደረገው ጥናት ላይ ተመሥርቶ ወደ ዘርፉ መግባቱን የድርጅቱ አመራሮች ገልጸዋል።

ጥናቱ በየዓመቱ ከ450 ሺህ እስከ 500 ሺህ የሚደርሱ ቤቶች እንደሚፈለጉ፣ ከዚህ አንጻር ግን የሚገነቡና ለተጠቃሚዎች የሚደርሱ ቤቶች አቅርቦት እጅግ ውስን መሆኑን አመልክቷል።

ይኸውም በየዓመቱ የሚጀመሩ ግንባታዎች 50 ሺህ አካባቢ ሲሆን ተገንብቶ የሚጠናቀቀው ግን 5 ሺህ አካባቢ ነው፡፡

ይህም የጠቅላላው 10 በመቶ አካባቢ ሲሆን፣ ከዚያም ውስጥ ለነዋሪዎች ተደራሽ የሚደረገው አንድ በመቶ ብቻ መሆኑን ይኸው ጥናት ማረጋገጡን የድርጅቱ ኃላፊዎች አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ ይህን ጨምሮ በዘርፉ ካሉ ክፍተቶች መካከል በተለይ የፕሮጀክቶች የርክክብ መዘግየትን እንደ ዋነኛ ችግር መለየቱን ገልጿል፡፡

በዚህም የተነሳ ሁዳ ኢንጅነሪንግ ለደንበኞች በሚገባው ቃል መሠረት በተባለው ጊዜ ማድረስን የድርጅቱ ዋነኛ መርሕ አድርጎ ይዟል።

ይህንን ለማሳካት በዚህ ረገድ ከሚደነቁና በፍጥነት ከሚያስረክቡ ሀገራት መካከል ዱባይና ቻይና ልምድ ተቀስሟል፡፡

በዚህ መሠረት የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ የአሠራር ዘዴን መጠቀም መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በዚህ አሠራር መሠረት የፕሮጀክቶችን መዋቅራዊ ሥራ በስድስት ወራት፣ ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን ደግሞ በቀጣዮቹ አንድ ዓመት ውስጥ በማጠናቀቅ፣ በአጠቃላይ ሁለት ዓመት የሚፈጅ ፕሮጀክትን በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ለደንበኞች ማስረከብ እንደሚቻል በጥናት መድረሱን የድርጅቱ ማርኬቲንግ ማኔጀር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ድርጅቱ እስከ አሁን በሪል እስቴት ዘርፍ አምስት ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን፣ በቡልቡላ የሚገኙ ሁለት ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለነዋሪዎች አስረክቧል።

በቦሌ የሚገኘውን የአደይ ፕሮጀክት ደግሞ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ማጠናቀቅ ችሏል።

በተጨማሪም የኒያላ ሞተርስ ፕሮጀክትን መዋቅራዊ ሥራ በዘጠኝ ወራት አጠናቆ የቀሪ የግንባታና የማጠናቀቂያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ በሪል ስቴት ዘርፍ መሳተፍ ከጀመረበት ወቅት አንስቶ በነበሩ ዓመታት አራት ኪሎ ላይ የመኖሪያ ሕንጻ፣ መርካቶ ለሱቅ የሚሆን ሕንጻ፣ እንዲሁም ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን በሀያት፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ አጣና ተራ እንዲሁም ጦር ሃይሎች ላይ ይዟል።

ሃያ አራት አካባቢ ደግሞ በአካባቢው ያለውን ትንሹን ስታድየም በማማከር ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ታውቋል፡፡

ሁዳ ኢንጂነሪንግ በሥራው ሂደት የቦታ ምርጫን፣ የግንባታ ጥራትንና በጊዜ ማስረከብን የማይደራደርባቸው ሦስት ዋነኛ መርሖዎቹ እንደሆኑ ገልጿል።

የግንባታ ግብዓቶችን በተለይም ብረትን በጊዜ ማግኘት በዘርፉ ከሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች አንዱ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህንንም ለመቅረፍ ፕሮጀክቶችን ከመጀመሩ በፊት የሚያስፈልጉ የብረት ግብዓቶችን ከውጭ አስመጥቶ በማዘጋጀት እንደሚሠራ አመልክቷል።

በተጨማሪም በሪል እስቴት ዘርፍ የፕሮጀክቶችን ብዛት ከማብዛትና ከማራዘም ይልቅ አንዱን ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ ወደ ቀጣዩ የመሸጋገር አሠራርን እንደሚከተል አስታውቋል።

ሁዳ ኢንጂነሪንግ ከግንባታ ሥራዎች በተጨማሪ የዲዛይን፣ የማማከርና የቁጥጥር አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሂባ አርክቴክት የተባለ እህት ኩባንያም አለው።

ድርጅቱ በመኖሪያና በንግድ ሕንፃዎች ግንባታ ላይ የሚሠራ ሲሆን፣ በተለያዩ የግልና የመንግሥት ተቋማት ጋር በመሥራት ያካበተውን የምህንድስና ልምድ በራሱ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚተገብር ገልጿል።

የድርጅቱ አመራሮች በበኩላቸው፣ የዛሬው የቁልፍ ርክክብ የቤቶችን ግንባታ ከማጠናቀቅ ባለፈ ለደንበኞች የተገባውን ቃል የመፈጸም ብቃትን የሚያሳይ መሆኑን በመግለጽ፣ በቀጣይም በቦታ ምርጫ፣ በጥራትና በወቅቱ ርክክብ ላይ በማተኮር ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- ድሬቲዩብ

Tags: Huda Engineering PLCHuda Propertiesሁዳ ፕሮፐርቲስ
Previous Post

የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

Next Post

በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

ቴምር ሪል እስቴት በጋርመንት አካባቢ ያስገነባውን ዘመናዊ ባለ 20 ፎቅ ህንፃ ለንግድ ሱቅ ደንበኞቹ አስረከበ
Property Handover

ቴምር ሪል እስቴት በጋርመንት አካባቢ ያስገነባውን ዘመናዊ ባለ 20 ፎቅ ህንፃ ለንግድ ሱቅ ደንበኞቹ አስረከበ

October 24, 2026
ፕራይም ሪል እስቴት ከውል ጊዜው ቀድሞ ያጠናቀቀውን የቦሌ ሚሊኒየም ፕላዛ አፓርትመንት አስመረቀ
Property Handover

ፕራይም ሪል እስቴት ከውል ጊዜው ቀድሞ ያጠናቀቀውን የቦሌ ሚሊኒየም ፕላዛ አፓርትመንት አስመረቀ

October 13, 2026
ዝቋላ ሪል እስቴት በሲኤምሲ ያስገነባውን “ሂል ሳይድ አፓርትመንት” ለቤት ባለቤቶች አስረከበ
Property Handover

ዝቋላ ሪል እስቴት በሲኤምሲ ያስገነባውን “ሂል ሳይድ አፓርትመንት” ለቤት ባለቤቶች አስረከበ

September 20, 2026
Next Post
በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
ቴምር ሪል እስቴት ሦስት አዳዲስ የግንባታ ሳይቶችን አስተዋወቀ

ቴምር ሪል እስቴት ሦስት አዳዲስ የግንባታ ሳይቶችን አስተዋወቀ

November 22, 2026
በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

በረካ ሪል እስቴት ከ14 በላይ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማከናወኑን ገለጸ

November 22, 2026
ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

ሁዳ ፕሮፐርቲስ በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች አስረከበ

November 22, 2026
የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

የፍሊንትስቶንስ አፓርትመንቶች በሐራጅ ተሸጠው ለቀድሞ ደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዘዘ

November 21, 2026
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (21)
  • Legal Updates (90)
    • Community Complaints (9)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (17)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (14)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (68)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent