ጊፍት ሪል እስቴት ከዛሬ ሰኔ 13 ጀምሮ እስከ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አራተኛውንና የመጨረሻውን ዙር ቤቶች ሽያጭ ማካሄድ መጀመሩን አስታውቋል።
ጊፍት ሪል እስቴት በ2% ቅድመ ክፍያ እስከ ከ15% -25% ልዩ ቅናሽ በማድረግ ልዩ የአፓርትመንትና የንግድ ሱቆችን ሽያጭ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለትም አራተኛውን ዙር ቤቶች ሽያጭ ማካሄድ ጀምሯል።
በዚህ አራተኛው ዙር የቤቶች የሽያጭ ኤክስፖ እስከ 25% ቅናሽ መደረጉ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲ ኤም ሲ እና በፈረስ ቤት ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮች እየገነባ ይገኛል፡፡ በመንደሮቹ ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል ተብሏል፡፡
ድርጅቱ የደንበኞችን ፍላጎትና ከጊዜው ጋር ተመራጭ የሆነ ዲዛይንና አዳዲስ እሴቶችን በማካተት ከዚህ ቀደም ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ ድሬቲዩብ


















