ይህ ቤት ይገኝ የነበረው ቦሌ ወሎ ሰፈር ወደ ቄራ መታጠፊያው መንገድ አካባቢ ላይ ነበር፡፡
ይህን ቤት ሁለት ግለሰቦች የይገባኛል ጥያቄ አንስተው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤትም ወስደውት ላለፉት 23 ዓመታትም ክርክሩ በሂደት ላይ ነበር ተብሏል፡፡
ክርክሩ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ሊወስድ ቻለ በሚል ለተነሳው ጥያቄ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የህግ ባለሙያ ጉዳዩ በእርግጥም ውስብስብ ችግሮች እንደነበሩበት ተናግረዋል፡፡
የክስ ሂደቱ መቋጫ ሳያገኝ የተንዛዛው ይህ ክርክር አሁን ላይ በኮሪደር ልማት ምክንያት ቤቱ መፍረሱን ከህግ ባለሙያዎች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ምንጭ፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም


















