ዘጸዓት የለውጥ ሪል እስቴት ገንዘባችን ተበልተናል ቤቱን የውኃ ሽታ ሆኖ መቅረቱ ነው ሲሉ ዛሬ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም የዘጸዓት የለውጥ ሪል እስቴት ተመዝግበው የቤት ባለቤት ለመሆን ሲጠባበቁ የነበሩ ግለሰቦች መግለጫ ሰጥቷል።
መጋቢ አጥናፉ አመያ የዘጸዓት የለውጥ ሪል እስቴት የቦርድ አመራር ናቸው በመግለጫው ላይ የተፈጠረውን ሲያብራሩ ሪል እስቴቱ መጀመሪያ ሲቋቋም በቦርድ የሚመራ ሆኖ ሳለ እኛ በማናውቀው ሁኔታ ወደ ፒኤልሲ ተቀይሮ ሐዋርያው ማቲዎስ ያቆብ እንደፈለጉ የሚያደርጉት የግል ንብረታቸው ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የሪል እስቴቱ የባንክ አካውንት ውስጥ ገንዘብ የለም፤ ቤቱ ይቅርብኝ ገንዘቡን መልሱልኝ ያለ ግለሰብ የሚያስተናግደው የለም፤ የተጀመረም የቤት ግንባታ የለም፤ በአዲስ አበባ በድርጅቱ ስም የተመዘገቡ ሶስት መሬቶች አሉ አሁን እንዳይሸጥ ብለን አሳግደናል፤ ወደ ፒኤልሲ የዞረው ድርጅት ወደ ቦርድ እንዲመለስ ከነሃሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሽምግልና ለመጨረስ የተጀመረው ሙከራ ተጓቶ የተለያዩ ሰበብ እየተፈጠረ ሊሳካ አልቻለም፤ መንግስት የህዝቡን ገንዘብ ለማስመለስ የምናደርገው ጥረትን እንዲተባበር ሲሉ የቦርድ አመራር የሆኑት መጋቢ አጥናፉ ተናግሯል።

በርካታ ሰዎች በሚሊዮን ያስገቡት ገንዘብ ኦዲት ሲደረግ 15ሺህ ብር ተብሎ በድርጅቱ ሰነድ ውስጥ ተመዝግቦ እንደተገኘ ተገልጿል።
የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢዎች አራት አመት ሆኖናል ያሉት ቤት ተመዝጋቢዎች እስካሁን ምንም ነገር የለም ብሏል።
በአጠቃላይ ወደ አራት ሺህ ቤት ፈላጊዎች እንደገመዘገቡ የተገለፀ ሲሆን ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ በባህር ማዶ በቸርች ውስጥ በመገኘት እንድንመዘገብ ቅስቀሳ ሲደረግ ነበር ሁላችንም ገንዘባችንን ተበልተን ልንቀር ነው መንግስት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ተናግሯል።


















