በውይይቱ ወቅት አንዳንድ አልሚዎች ወደ ስራ መግባታቸው የተገለፀ ሲሆን በተለያዩ ምክንያት ጋር ተያይዞ ችግር ገጥሟቸው ወደ ስራ ያልገቡ አልሚዎች ችግራቸው ተፈቶ በአስቸኳይ ወደ ስራ እንዲገቡ በውይይቱ ተነስቷል።

በተጨማሪም በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ስራን ከስራ ፈላጊው ጋር በማገናኘት ስራዎች በተገቢው መንገድ ስራውን በሚሰራው ሰው እንዲፈፀም የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን በማንሳት ለስራውም የሚፈለገው የሰው ሀይል በቁጥር ሆነ በማህበር ደረጃ የተለየ ሲሆን አልሚዎችም ትክክለኛ ስራ ፈላጊዎችን ከሚያደራጀው አካል ጋ በመነጋገር ወደ ስራ በማስገባት ውላቸውን ተፈፃሚ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች እና የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል አጋርነት/PPP/ ተወካዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በስተመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት እና የአልሚ ድርጅት ተወካዮች የስራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ በተዘጋጀው የስምምነት ሰነድ ላይ ተፈራርመዋል።
Soource: አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

















