በዱባይ እና አካባቢው የሪል እስቴት ሽያጭ እያከናወነ የሚገኘው ራምዚን ሪል እስቴት ለሜሪ ጆይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስር ለሚገኙ 100 ህፃናት እና አረጋውያን በየወሩ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ።
የራምዚን ሪል እስቴት ባለቤት አቶ አህመድ ዚናብ የሜሪ ጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ስለጎበኘቻቸው ምስጋና አቅርበው “እንደ እናነተ ያሉ ተቋማት መጠየቅ ሳይሆን መጠየቅ ነው ያለባቸው። በየወሩ መቶ ሰዎችን እንረዳለን” ብለዋል።

አንድ ዲያስፓራ ለ አንድ ጎዳና ተዳዳሪ በሚል ንቅናቄ ከአርቲስቶች ጋር ዱባይ እንደተገኙ የገለፁት ሲስተት ዘቢደር በበኩላቸው ራምዚን ለተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን፣ ለሜሪ ጆይ ለተደረገው ድጋፍ በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል።


















