የኢትዮጵያ መንግሥት “የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ” የሚፈቅድ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች ቤት እንዲገዙ የሚፈቅደው ሕግ ዝግጅት “የመጨረሻው ደረጃ ላይ” እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሌላቸው በቀር የንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚከለክለው አሰራር እንደሚቀየር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተናገሩት “ታማኝ” ከተባሉ ግብር ከፋዮች መካከል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።


















