• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result

የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ

Betegna Team by Betegna Team
October 10, 2024
in Proclamations (አዋጅ)
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ግንባታ ከማከናወናቸው አስቀድመው ቤት የሚሸጡ ሪል እስቴት አልሚዎች፤ ከደንበኞቻቸው የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ የባንክ አካውንት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

አዲሱ የሪል እስቴት ልማት ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል?

  • ሪል እስቴት አልሚዎች፤ ያልገተነባ ቤት መሸጥ የሚችሉት ከመንግስት ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ነው።
  • አልሚዎች፤ ያልተገነባ ቤት በመሸጥ የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት ለማስቀመጥ ይገደዳሉ።
  • የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ አልሚዎች፤ ደንበኞችን መመዝገብ እና ክፍያ መሰብሰብ አይችሉም።
  • ደንበኞች ካልፈቀዱ በቀር ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤትን ማስረከብ ይከለክላል።
  • በብዛት ከገነቡት ቤት ውስጥ 40 በመቶውን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የሚያቀርቡ አልሚዎች፤ መሬት “በስፋት” ይቀርብላቸዋል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል እስቴት አልሚዎች ደንበኞችን እንዳይመዘግቡ እና ቅድመ ክፍያ እንዳይሰበስቡም ይከለክላል።

“የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ” የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ሐሙስ መስከረም 30/2017 ዓ.ም. በተደረገው የፓርላማው አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በዛሬው ስብሰባ ላይ ከቀረቡት ስድስት ረቂቅ ሕጎች መካከል የሆነው ይህ አዋጅ፤ ከዚህ ቀደም ራሱን የቻለ ሕግ ላልነበረው የሪል እስቴት ቤቶች የግንባታ እና ግብይት ሂደት አዲስ እና አሳሪ አሠራሮችን ያስተዋወቀ ነው። እንደ ሕንጻ ያሉ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ያላቸው ዋጋ በመንግሥት እንዲሁም በግል ባለሙያዎች የሚገመትበት እንዲሁም ግመታው አገልግሎት ላይ የሚውልበት አሠራርም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።

በኦቪድ ግሩፕ በአቃቂ ቃሊቲ የሚገነባው 60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ዲዛይን

ከረቂቅ አዋጁ ጋር አብሮ ለምክር ቤቱ የቀረበው ማብራሪያ የሪል እስቴት ልማት፣ ግብይት እና የዋጋ ትመና “በቂ የሕግ ሥርዓት የሌለው በሕገወጥ ደላሎዎች ተጽዕኖ ስር የወደቀ” እንደሆነ ያስረዳል። የሪል እስቴት ልማት ካለው የቤት ፍላጎት “በእጅጉ የራቀ” እንዲሁም “በሕገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ደላላ ተብለው በሚታወቁት አካላት” ተፅዕኖ ስር የወደቀ እንደሆነ በማብራሪያው ላይ ሰፍሯል።

አዋጁን ማዘጋጀት አስፈላጊ ከሆነባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ፤ “ቤት ለመግዛት እና ለመከራየት የሚፈልጉ ወገኖች በከፍተኛ ሁኔታ የሚቸገሩበት ሁኔታ መቀየር ስላለበት የሪል እስቴት ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና የቤት አቅርቦት እንዲሻሻል መደገፍ ማስፈለጉ” እንደሆነም ተጠቅሷል።

በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል እስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ “የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ” የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል እስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን እንዳለባቸው በረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

የአገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች ግንባታውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን “የፋይናንስ አቅርቦት ምንጭ” የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦባቸዋል። ይሁንና ረቂቁ፤ “የቅድሚያ ቤት ሽያጭ ተጠቃሚነት” መብትን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰጥቷል።

ይህ አሠራር የሪል እስቴት አልሚዎች የቤት ግንባታውን ሳያከናውኑ ወይም በሂደት ላይ እያለ ለግንባታው የሚውልን ፋይናንስ የሚያሰባስቡበት እና ገንዘቡን ለግንባታው የሚያውሉበት መንገድ ነው። የቤት ግንባታው ሳይከናወን በፊት ከገዢዎች ጋር ውል ማሰር እና ክፍያ መፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በሪል እስቴት ልማት ላይ በተሰማሩ አልሚዎች በኩል የተለመደ አሰራር ነው።

ጊፍት ሪል እስቴት ለገሃር አካባቢ እየገነባ የሚገኘው የሞኖሪያ መንደር ዲዛይን

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ በዚህ ዓይነት መልኩ ለግንባታ የሚውለውን ሀብት ማሰባሰብ የሚፈልጉ አልሚዎች “አግባብ ካለዉ አካል ፈቃድ ማቅረብ” እንደሚጠበቅባቸው ያስረዳል። ረቂቁ፤ “የሪል እስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመሥራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካል አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት [አለበት]” ሲል አዲሱን ግዴታ አስቀምጧል።

የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል እስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል። አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ “የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ” እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።

ገንዘቡ የሚቀመጥበት ዝግ የባንክ አካውንት የሚከፈተው “አግባብ ባለው አካል ፈቃድ መሠረት” እንደሆነም አዲሱ ሕግ ያስረዳል። በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚወጣ ደንብ እንደሚወሰንም ተጠቅሷል።

ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት መሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ “በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ” እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል። ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል እስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት “ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ” እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።

ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ በሪል እስቴት አልሚዎች ላይ ሌሎች ግዴታዎችንም ጥሏል። በረቂቁ መሠረት፤ የሪል እስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።

ረቂቁ፤ “ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም” ሲል ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቀ ቤት ለማስረከብ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል። ሪል እስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።

አልሚዎች ምዝገባ ማድረግ እና ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉት “የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከተረከቡ” በኋላ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ተካትቷል። “በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም” የሚለውም ሪል እስቴት አልሚዎች ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች መካከል ነው።

ለሪል እስቴት ልማት አሠራር የሚዘረጋው አዲሱ አዋጅ፤ ከግዴታዎች ባሻገር አልሚዎች ከመንግሥት “መሬት በስፋት” ማግኘት የሚችሉበትን ሂደትም ያስቀመጠ ነው። ከመንግሥት መሬት “በስፋት” የሚቀርብላቸው አልሚዎች ረቂቁ ላይ ከተጠቀሱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በብዛት ቤቶችን መገንባት እና ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ “40 በመቶውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ” ማድረግ የሚለው አንዱ ነው። ይህንን ቅድመ ሁኔታ የሚከተሉ አልሚዎች የሚገነቡት ቤት ብዛት “እንደ ከተሞች ደረጃ በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ አምስት ሺህ” ሊሆን እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተጠቅሷል።

መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት “በስፋት” የሚያቀርበው “በአዲስ አበባ ከ5 ሺ በላይ ቤት ለሚገነባ እና ለሚያስተላልፍ” አልሚ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል። በሌሎች ከተሞች መሬት “በስፋት” የሚቀርበው እደሚኖራቸው “ተጨባጭ የቤት ፍላጎት” ሲሆን፣ “ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባሉ ከተሞች” ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች እንደሚቀርብላቸው ረቂቁ ያስረዳል።

ከመንግሥት መሬት “በስፋት” ማግኘት የሚፈልጉ አልሚዎች የተቀመጠባቸው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተገናኙ ናቸው።

በአገር ውስጥ “በጥራት እና በብዛት የማይገኙ” ግብአቶችን በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (ፍራንኮ ቫሉታ) የሚያስገቡ እንዲሁም የሚያገኙትን ትርፍ እስከ አስር ዓመት ከአገር ሳያወጡ አገር ውስጥ መልሰው የሚጠቀሙ አልሚዎች የዚህ አሠራር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

“የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ” የተሰኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተጨማሪ ዕይታ ወደ ከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል።

ምንጭ፦ BBC NEWS አማርኛ

ሙሉን የአዋጅ ቅጅ ከታች አያይዘናል።

የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅDownload
Tags: draft proclamationEthiopia mortgage lawEthiopia property lawEthiopian parliamentReal Estate Developmentreal estate Ethiopiareal estate policy
Previous Post

የቀበሌና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Next Post

ኦቪድ ሪል እስቴት ከሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ከሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አዋጅ ጸደቀ
Proclamations (አዋጅ)

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አዋጅ ጸደቀ

July 1, 2025
በኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች በሊዝ የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ በነገው ዕለት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው
Proclamations (አዋጅ)

በኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች በሊዝ የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ በነገው ዕለት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው

May 20, 2025
የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
Proclamations (አዋጅ)

የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

December 5, 2024
Next Post
ኦቪድ ሪል እስቴት ከሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ከሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

ኦቪድ ሪል እስቴት ከሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ከሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent