በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብርካሳ እና 100 ሄክታር ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።
- በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ ፦
- 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣
- 10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች
- 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500 የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በ8 ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር ቦታ ለማልማት ተቅዷል ብለዋል።
የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የትኞቹ ናቸው ?
- ካሳንቺስ- እስጢፋኖስ-መስቀል አደባባይ- ሜክሲኮ- ቸርችል-አራት ኪሎ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ (የኮሪደሩ ርዝመት 40.4 ኪ/ሜ)
- ጫካ ፕሮጀክት (ሳውዝ ጌት)- መገናኛ- ሃያ ሁለት- መስቀል አደባባይ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 7.1 ኪ.ሜ)
- ሲኤምሲ- ሰሚት- ጎሮ- ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል ኮሪደር እና የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 10.8 ኪ.ሜ)
- ሳር ቤት- ካርል አደባባይ- ብስራተ ገብርኤል- አቦ ማዞሪያ- ላፍቶ አደባባይ- ሃና ፉሪ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 15.9 ኪ.ሜ)
- አንበሳ ጋራዥ- ጃክሮስ- ጎሮ ኮሪደር ( የኮሪደሩ ርዝመት 3.1 ኪ.ሜ)
- አራት ኪሎ- ሽሮ ሜዳ- እንጦጦ ማርያም- እጽዋት ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 13.19 ኪ.ሜ)
- ቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 20 ኪ.ሜ)
- እንጦጦ-ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 21.5 ኪ.ሜ)
በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል።

















