የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ እና የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ቢሮው ለኪራይ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) በኦንላይን (https://addishousebid.gov.et/ ሲስተም ወይም በአካል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 1፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል፣ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ቦታዎች ድጋፍ በማግኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ



















