የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ:-
- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በ 4ኪሎ ፕላዛ ውስጥ የሚገኙ 24 የንግድ ቤቶችን በኢትዮጵያ ብር
- በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሾላ ገበያ በየካ 2 የመኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙ 16 የንግድ ቤቶችን በኢትዮጵያ ብርእንዲሁም
- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሳርቤት ፕላዛና ፓርኪንግ ውስጥ የሚገኙ 70 የንግድ ቤቶችን በ ዶላር በጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ቢሮው ከግንቦት 4/2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰንዱን እየሸጠ የሚገኝ ሲሆን ማንኛም ፍላጎቱ ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታውን ሰነድ በዌብሳይት www.addishouse.bid.gov.et ኦንላይን በመግባት አስፈላጊውን ምዝገባ በማድረግ በቴሌብር የማይመለስ 700 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን
ከዚህ በተጨማሪም ሰነዱን በአካል ቀርበው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች 6ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባት ስራዎች ቢሮ 11ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል፣ በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች የቤቶች የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጥዋቱ 1 ሰአት እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጥዋቱ 1 ሰአት እስከ ቀኑ 6:30 ተጫራቾች ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ምንጭ፡ አዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ


















