መንግስታዊዉ ነዳጅ አቅራቢ የሆነዉ ድርጅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚያደርግበትን ግዙፉን ህንፃ ለመገንባት የኮንትራት ዉል ስምምነት ማድረጉ ታዉቋል።
በአቃቂ የሚገነባው 2B+G+14 ስማርት የችርቻሮ ጣቢያ ዋና መስሪያቤት በ 24 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ካፒታል ሰምቷል።
ኢኢአይጂ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የዉል ስምምነት ያደረገው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አማካሪ ነዉ።

















