ፐርፕዝ ብላክ ኢትኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር የተሰኘው ድርጅት በዋስትና ያስያዛቸው ንብረቶች ለሐረጅ ጨረታ ቀረቡ፡፡
ብርሃን ባንክ አስክሲዮን ማኅበር ማስታወቂያ ያወጣባቸው ንብረቶች፣ ድርጅቱ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች በሐራጅ መነሻ ዋጋ አቅርቧቸዋል፡፡
ብርሃን ባንክ ለጨረታ ያቀረባቸው ግዙፍ ማሽነሪዎች ብዛታቸውም 13 ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ማሽነሪዎች ሲሆኑ ከአራት እስከ ሰባት ሚሊዮን ብር በሚደርስ መነሻ ዋግ ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡት አብዛኛዎቹ ማሽነሪዎች ቀረጥ ያልተከፈለባቸው ሲሆኑ የግብርና ትራክተሮችና ሎደሮች ይገኙበታል፡፡
ፐርፐዝ ብላክ በወቅቱ ግምታዊ ዋጋው, ከአራት ዓመት በፊት, 60 ቢሊዮን ብር የሆነ “ከገበሬው” የተሰኘ ሕንፃ ሜክሲኮ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ፋብሪካ ቦታ ላይ ለመገንባት የአክሲዮን ሽያጭ ፈጽሞ ነበር፡፡
ምንጭ፡ ሰሌዳ

















