ታዋቂው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ /ኃይሌ ዘ በቅሎ ቤት/ የ60ኛ ዓመት ልደት በማስመልከት ከታሜሶል ኮምኒኬሽንስ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ከበረ የ 3 ነጥብ 4 ሚልየን ብር ግምት ያለው የ BYD E 2 መኪና ስጦታ ተበርክቶለታል።
ጋዜጠኛ ደረጄ በተመሳሳይ ሁኔታ ከጃምቦ ሪልስቴት የመኖርያ ቤት ስጦታ መቀበሉና ለሶስት ዓመታት የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሆን መስማማቱ መገለፁ ይታወሳል።
ይህ ስጦታ እንዲሳካ በዋናነት የደከመችው አዜብ ወርቁ ምስጋና ቀርቦላታል። “ደርዬዋ ከነወዝህ ከነለዛህ ብዙ ዓመት ኑርልን” የሚል መልካም ምኞትም ተገልጾለታል።
የስጦታ ስነ ስርዓቱን የሚያሳየው ቪዲዮ ከታች ተያይዟል።


















