251 ኮሚዩኒኬሽን ኤንድ ማርኬቲንግ ኃላፊነቱ የሚያዘጋጀው አመታዊው “ኢቲ ሪል እስቴት እና ሆም ኤክስፖ” ለሰባተኛ ጊዜ ከዛሬ ከታህሳስ 18 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል።
በዘንድሮው ኤግዚብሽን ሻጩን እና ገዢውን ከማገናኘት ባለፈ የፖሊሲ አውጪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች ከአልሚዎች ጋር ተቀራርበው በቤት ልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ ያሏትን አድሎች ለመምከር እና በግሉ እና በመንግስት ዘርፍ ድልድይ ለመሆን በማለም “The future of Real Estate” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በ7ኛው አመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ላይ የሪል እስቴት አልሚዎች፣ ገዢዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በውይይቱ ላይ የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ ፀጋዬ ሞሼ(በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማትና አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ)፣ አቶ አሰፋ ሱሞሮ (በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ) እንዲሁም በአወያይነት አቶ ሙከሚል በድሩ ተሳትፈዋል።
ኤክስፖው እስከ እሑድ ታህሳስ 20/2017 በሸራተን አዲስ ይካሄዳል።


















