ከዚህ ቀደም በከተማችን “በጊዜ ግቡ!” በማለት የሚታወቀው ጀንቦሮ ሪል እስቴት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ጋር ዛሬ ጥር 2 ቀን 2016 በደረሰው የጋራ ስምምነት መሠረት በተለያዩ ዓለማት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በልዩ ቅናሽ ቤት ለመሸጥ ተፈራርሟል።
በስምምነቱም መሠረት ጀንቦሮ ሪል እስቴት ቦሌ ቡልቡላ 70 በመቶ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 100 ቤቶችን እንዲሁም ዲፕሎማቲከ ሰፈር በሆነው ሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሦስት ዓመት ውስጥ ተገንብቶ በሚጠናቀቀው ቅንጡው የኪሩ አፓርትመንት፣ 400 ቤቶችን ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር አባላት በልዩ ቅናሽ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር 2001 ዓ.ም የተቋቋመና በሥሩም ከ10,000 በላይ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ አባላት ያቀፈ ሲሆን፣ ማኅበሩ ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር በማገናኘት እንደ ድልድይ ከመሆኑም በተጨማሪ ለዳያስፖራው ድምፅ የሆነና እየሆነም ያለ ማኅበር ነው። ከዚህም በተጨማሪ ማኅበሩ በተለያየ አቅጣጫ የዳያስፖራውን ጥቅም የሚያስጠ ብቁ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ ወደፊትም መሰል አጋርነቶችን በማጠናከ ር የአባላቶቹን ፍላጎት ለማርካት እየተጋ ይገኛል።

ጀንቦሮ ከገነባቸውና እየገነባ ካላቸው ስድስት ፕሮጀክቶች ሦስቱን ያስረከበ ሲሆን በሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ እያስገነባ ያለው ኪሩ አፓርታማ ከመኖሪያ ቤት በዘለለ ጥሩ የሕይወት ዘይቤና ቅንጡ አኗኗርን ለሚመኙ ኢትዮጵያዊያን የመጀመሪያው አማራጭ ነው።
በ5,077 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ኪሩ ፕሮጀከት ሲጠናቀቅ፣ 30 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፡ ሰባት ወለል የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም አምስት ወለሎች ደግሞ ለዓለም አ ቀፍ ብራንድ ሱቆች በተጨማሪም 1.000 ካሬ ሜትር አረንጓዴ ስፍራ ይኖረዋል።

















