ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ሩታ መንግስትአብን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።
ተወዳጇ አርቲስት ሩታ መንግስትአብ ከዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ጋር በብራንድ አምባሳደርነት በሚሊዮኖች ብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረመች፡፡
ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የተለያዩ ቅንጡ የሆኑ አፓርትመንቶችን በከፍተኛ ጥራት በመሀል ከተማ እየገነባ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከሪል እስቴት ግንባታ ስራዎች ባሻገርም ከአስራ ስምንት ዓመታት በላይ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው እንደ አክሲስ ፋዉንዴሽን ስፔሻሊስት ኃ/የተ/የግል/ማህበር፣ ቪቶሪዮ ኬሚካል ኢንደስትሪስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር እና ሻይኒንግ ስቶን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር እህት ኩባንያ አሉት።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ አርቲስት ሩታ መንግስትአብም በተሰጣት እድል እና ክብር ከልብ መደሰቷን ገልፃ በሪል እስቴት ዘርፍ የራሳቸዉን አሻራ ለማሳረፍ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ድርጅቱን በብራንድ አምባሳደርነት እንድታስተዋዉቅ በመመረጧ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
ምንጭ፦ Dire Tube


















