አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ በ10 አመት ውስጥ 150 ኩባንያዎችን ለማቋቋም እየስራ እንደሚገኝ ገልጿል። ከዚህ መካከል አንዱ በሆነው ጎዶ ሃውሲንግ ኤንድ ስማርት ሪል እስቴት የመንግስትና የግል አጋርነት 70/30 እሴትን ከአፍሪካዊ ማንነታችን ጋር አጣምሮ እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ጥር 28/2017 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤታቸው በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
ጎዶሃውሲንግ ኤንደ ስማርት ሪል እስቴት ቤቶችን ከ50ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ለማድረግ በሰንጋተራና በተክለሃይማኖት መካከል ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት በአስር ሺ ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ለመኖርያ ቤትና ለሱቆች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ኤክስፖ አዘጋጅቷል።
አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ከተመሰረተ ሶስት ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረ ሲሆን 150 ድርጅቶች በጋራ እያቋቋመ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ምንጭ፡ FastMereja


















