የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን በማኅበር ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያዘጋጀውን መመሪያ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ደርሶናል፡፡
በመሆኑም በዱባይ እና ሰሜን ኤምሬቶች በሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የምትኖሩ እና በውጭ ምንዛሪ (በዶላር) አገር ቤት መቆጠብ የምትችሉ ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ የክልሉ ተወላጆች የዳያስፖራው ማህበረሰብ 12 ወይም 24 በመሆን በማኅበር በመደራጀት በሸገር ከተማ በተዘጋጀው የቤቶች ልማት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።
የመኖሪያ ቤቱን ደረጃ እና የሚከፈለውን ገንዘብ ግምት ከዚህ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከቆንስላው የዳያስፖራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 20 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በዱባይ እና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት


















