6ኛው ዙር የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ ውጤት ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1735 ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ከሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አየር ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ለጨረታ ከቀረቡ ንግድ ቤቶች መካከል ከዚህ በታች በቀረበው ሰንጠረዥ የተገለጹ 419/አራት መቶ አስራ ዘጠኝ/ ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ሆነው የተለዩ መሆኑን እየገለጽን፣ ይህን ጨረታ ለማስፈጸም በወጣው የተጫራቾች መመሪያ ክፍል ሁለት አንቀጽ 28 “የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉን በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ10/አስር/ የቅሬታ ማቅረቢያ የስራ ቀናት በኋላ የተለዩ አሸናፊዎች ተቋሙ ጥሪ ከሚያደርግበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ውል የማዋዋያ ቦታ በመገኘት የንግድ ቤት የሽያጭ ውል መፈፀም አለበት፡፡” ተብሎ በተደነገገው መሠረት ተፈጻሚ የሚደረግ መሆኑን ታውቆ በጨረታ ውጤቱ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዚህ ጉዳይ ለተቋቋመው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በፅሁፍ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን


















