ኦቪድ ሪል እስቴት ከሕዳር 22 እስከ ታሕሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አምስት የተለያዩ ቦታዎች ለ15 ቀናቶች የሚቆይ ታላቅ የሽያጭ ኤክስፖ ማዘጋጀቱን የኦቪድ ሪል እስቴት ማርኬቲንግ ማኔጀር ወ/ሮ መቅደስ ቀደመ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት በገርጂ ፊደራል ቤቶች ኦቪድ ግቢ ውስጥ፣ በገላን ጉራ ሳይት፣ በአራት ኪሎ ጥይት ቤት ሳይት፣ ኢትዮ ኩባ አዳራሽ እና ጎልፍ ክለብ ኤክስፖው የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል።
“ኦቪድ ሪል እስቴት በሥሩ በሚገኙት ኩባንያዎች በድምሩ ከ10 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ግዙፍ ኩባንያ ሲሆን፤ በታማኝ ግብር ከፋይነት ለአገራዊ ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ በተደጋጋሚ ለሽልማት የበቃ ተቋም ነው” ሲሉም ገልጸዋል።
ኦቪድ ሪል እስቴት ‘አልሙኒየም ፎርምወርክ’ የተባለውን ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በገርጂ የፌዴራል ኮርፖሬሽን ቤቶች ፕሮጀክት 500 ቤቶችን እንዲሁም በተቋማዊ የማህበራዊ ኃላፊነት ፕሮጀክቶች ደግሞ 205 ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማስረከቡን ገልፀዋል።
የተለያዩ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆች በቅናሽ ዋጋ ለሽያጭ የሚቀርቡ ሲሆን በዚህም መሰረት አመቺ የክፍያ ስርዓቶች በአማራጭነት መቅረባቸው ተመላክቷል።
ምንጭ: Arts Tv World


















