አትሌት ገንዘቤ ዲባባ «ገንዘቤ ዲባባ ፕሮፐርቲስ» የተሰኘ የሪል እስቴት ኩባንያ በመስረት ዘርፉን ተቀላቀለች።
በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረክ የደመቀ ታሪክና በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለችው ታዋቂዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ፣ በኢትዮጵያ እያደገ ወደሚገኘው የሪል እስቴት ዘርፍ በይፋ መግበቧን አስታወቀች።
አትሌቷ «ገንዘቤ ዲባባ ፕሮፐርቲስ» (Genzebe Dibaba Properties) በሚል ስያሜ አዲስ የቢዝነስ ተቋም በማቋቋም በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ አቅጣጫ ይዞ ለመስራት መዘጋጀቱን ይፋ አድርጋለች።
ተቋሙ የብዙዎችን የመኖሪያ ቤት ህልም እውን ለማድረግ አልሞ የተነሳ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ተመራጭ ቦታዎች ላይ ጥራታቸውን የጠበቁና ዘመናዊ የቤት ልማቶችን እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
ኩባንያው ይፋ ባደረገው ራዕይ፣ በስፖርቱ ዓለም የነበረውን የጽናት፣ የትክክለኛነት (Precision) እና የታላቅነት እሴቶች ወደ ግንባታና ዲዛይን ዘርፍ በማምጣት አዲስ የአሰራር ፍልስፍና እንደሚያስተዋውቅ አመልክቷል።
የብሪቲሽ ኤምባሲ አካባቢ ቅይጥ ግንባታ ፕሮጀክት (Mixed-Use Development)
ኩባንያው የመጀመሪያውን ሁለገብ (Mixed-use) የሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው ታዋቂ የዲፕሎማቲክ ኮሪደር ላይ በይፋ አስጀምሯል።

የክፍያ ቅናሽና ማበረታቻ፡ በ15% ቅድመ ክፍያ የሚጀመር እና ቀሪውን እስከ 3 ዓመታት በሚደርስ የክፍያ ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችል አማራጭ ተዘጋጅቷል።
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፖርቱ ያሳየችውን ጽናትና ትጋት ወደዚህ አዲስ የህይወት ምዕራፍ በማምጣት፣ የጀመረችው አዲስ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን መላው ደንበኞችና ወዳጆቿ ከጎኗ እንዲሆኑ ጥሪዋን አስተላልፋለች።


















