ጊፍት ሪል እስቴት በዛሬው እለት መጪውን የ2019 የአዲስ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ “መኖር በጊፍት መንደር!” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ነሀሴ 27 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የጊፍት ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትማዎች እና የንግድ ሱቆች የሽያጭ ኤክስፖ መክፈቻ ስነስርዓት አካሄዷል፡፡
ጊፍት ሪል እስቴት በ2% ቅድመ ክፍያ እስከ 20% ልዩ ቅናሽ በማድረግ ልዩ የአፓርትመንትና የንግድ ሱቆችን ሽያጭ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለትም ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት የሚቆይ የአዲስ አመት በዓል የቤቶች የሽያጭ ኤክስፖ ማካሄድ መጀመሩንም ገልጿል፡፡
በዚህም የአዲስ አመት በዓል የቤቶች የሽያጭ ኤክስፖ በ2% ቅድመ ክፍያ የ18% ቅናሽ መደረጉ የተነገረ ሲሆን ለዚህም 1500 ቤቶች ለሽያጭ ቀርበዋል ተብሏል፡፡
ጊፍት ሪል እስቴት በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮጀክት 12 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት በተያዘው ስምምነት መሰረት ከዚህ ቀደም “መኖር በጊፍት መንደር” የሽያጭ ኤክስፖ መርሃ ግብር ማካሄዱ ይታወሳል፡፡
የበዓል ቅናሹ በአሁኑ ወቅት በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በአትላስ ፣ በሲ ኤም ሲ እና በፈረስ ቤት እየገነባቸው ባሉት ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮች ላይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በመንደሮቹ ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል ተብሏል፡፡
በአሁኑ ሰአት 900 ቤቶችን ሰርቶ አጠናቅቆ ለደንበኞች ለማስረከብ ከጫፍ መድረሱንና በመጪው አመትም ወደ 2000 ቤቶችን ለደንበኞች ለማስረከብ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
ጊፍት ሪል እስቴት ለ600 ቋሚና የኮንትራት ሰራተኞች ሲጨመሩ ለ1000 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡
ጊፍት ሪል እስቴት ከተመሰረተበት ከ2005 ጀምሮ የደንበኞችን ፍላጎትና ከጊዜው ጋር ተመራጭ የሆነ ዲዛይንና አዳዲስ እሴቶችን በማካተት ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች እያስረከበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ምንጭ:-ድሬ ቲዩብ
















