ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት የ2026 ዓመታዊ መርሃ ግብሩን እና የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መቀበያ በዓሉን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል((Ethiopian Skylight Hotel)) የድርጅቱ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና አጋሮች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አከበረ።
ታዳሚዎቹ በነጭ ልብስ አምረውና ደምቀው በአደይ አበባ ምንጣፍ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ በበዓሉ ላይ የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደሮች የሆኑት ታዋቂዋ የፋሽን ሞዴል ሄላራ ተስፋዬ እና ታዋቂዋ ቲክቶከር የአብስራ አዲሱ ተገኝተዋል።
በዓመቱ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሽያጭ፣ የግንባታ፣ የሳይት መሪዎች እና የሥራ ባልደረቦች ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን፣ የዕለቱ ታላቅ ሽልማት የሆኑት የባለ 3 ክፍል መኖሪያ ቤት እና የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ተበርክቷል።
በዚህም መሠረት በቦሌ 24 አደይ አበባ ሳይት የሚገኝ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የባለ 3 ክፍል ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ለብርሃኔ ፍስሐ የተበረከተ ሲሆን፣ የ6 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ቢ.ዋይ.ዲ (BYD e7) የኤሌክትሪክ መኪኖች ደግሞ ለሁለት የሳይት ማናጀሮች ተበርክቶላቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ ባለሙያዎች የሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ባለፈው ዓመት ያስመዘገበውን ስኬትና የግንባታ እድገት ከመዘከር ባሻገር፣ ለአዲሱ ዓመት ያላቸውን እቅድ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በቦሌ አካባቢ የገነቧቸውን ፕሮጀክቶች በማስፋፋት «ቦሌ አደይ አበባ 2» እና «ቦሌ ሴንትራል 2» የተሰኙ አዳዲስ የቤት ፕሮጀክቶችን በይፋ አስተዋውቋል።
















