ታዋቂው ኮሜዲያን እና የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪ ያሲን በጉጉት የሚጠበቀውን 6ኛውን አርኪ ሆም ኤክስፖ ለማስተዋወቅ ከአርኪ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር የስራ አጋርነት ስምምነት ተፈራረመ።
በአዲሱ ዓመት ህዝቡ የሕልሙን ቤት ባለቤት እንዲሆን የሚያስችሉ አዳዲስ የሪል እስቴት አማራጮች እና ልዩ ቅናሾች ከያሲን ጋር በመሆን ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
ይህ በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው የአርኪ ሆም ኤክስፖ (Arki Real Estate Expo) ከመስከረም 8 እስከ 10 በጊዮን ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል።
ዝግጅቱ አዲስ ዓመትን አዲስ ጅምር ለማድረግ ለሚያስቡ እና ቤት ለመግዛት ለሚፈልጉ ሰዎች ምቹ አጋጣሚን ይዞ የቀረበ ነው።
በኤክስፖው ላይ የሚታደሙ ሰዎች አስተማማኝ ከሆኑ የሪል እስቴት አልሚዎች ጋር በአንድ ቦታ የመገናኘት ዕድል ያገኛሉ።
ይህም ለፍላጎታቸው እና ለአቅማቸው የሚሆን አዲስ ቤት መርጠው ለመውጣት የሚያስችላቸውን ቀላል እና ቀጥተኛ መንገድ የሚያመቻችላቸው ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ በጊዮን ሆቴል በመገኘት ዝግጅቱን እንዲጎበኙና የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
















