በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረትና ማቅረብ ዘርፍ ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ ልምድ ያለው ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስና ዘመናዊ ምርቶቹን ያስተዋወቀበት ደማቅ መርሃ-ግብር መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም በዑራኤል አከባቢ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ አካሄደ።
ድርጅቱ “ጥራት የመጨረሻው መድረሻችን ሳይሆን የማንደራደርበት መነሻችን ነው” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሮሜል ኤሌክትሪካል ቺፍ ማርኬቲንግ እና ሽያጭ ኦፊሰር እንደገለጹት፤ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት ከማሳደጉም በላይ የሀገር ውስጥ አቅርቦቱን በማጠናከር ምርቶቹን ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ በሰፊው እየሰራ ይገኛል።
በዕለቱ ከቀረቡት አዳዲስ በቴክኖሎጂ የበለፀጉ ምርቶች መካከል የፒያኖ ስዊቾች፣ ሶኬቶች፣ ብሬከሮች፣ ማግኔቲክ ትራክ ላይቶች፣ ሊነር ላይቶች፣ የኬብል ትራንኪንግ፣ ውኃ የማያስገቡ የኮርኒስ መብራቶች እና የማከፋፈያ ቦርዶች እንደሚገኙበት በመድረኩ ተገልጿል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙ እንግዶች በዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኙ ዘመናዊ ሾው ሩሞችንና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ምርቶችን የመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል።
ሮሜል ኤሌክትሪካል ለምርቶቹ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በሀገሪቱ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ምርቶችን ለማዘመንና ጥራታቸውን ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ መሰል የአጋርነት መድረኮችን በየዓመቱ እንደሚያዘጋጅም አስታውቋል።
ምንጭ፦ Fast Mereja


















