በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2018 ዓ.ም የቅን ልቦች ሜሪት ፕሮፐርቲስ የበጎ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የአሸናፊዎች አሸናፊ እንዲሁም በተስፋ ከተጣለባቸው የቅን ልቦች ውድድር ታላላቅ አሸናፊዎች በይፋ ታወቁ።
በዚሁ በሜሪት ፕሮፐርቲስ አስተባባሪነት በተካሄደው ታሪካዊ የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በማህበረሰብ በጎ አድራጎት እና አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ተለይተው የወርቅ ሽልማት የተጎናጸፉት አካላት ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በአሸናፊዎች አሸናፊዎች ምድብ አቲስነማ ቻሪቲ የቁጥር አንድነትን በማስመዝገብ የ100 ግራም ወርቅ ታላቅ ሽልማት ባለቤት ሆኗል።
በዚሁ ምድብ አዶናይ የ50 ግራም ወርቅ ተሸላሚ በመሆን ሁለተኛውን ደረጃ የጨበጠ ሲሆን አወንታ በርሲሳ ደግሞ የ30 ግራም ወርቅ ተሸላሚ በመሆን ሦስተኛ ደረጃ አሸናፊ መሆን ችሏል።
በሌላ በኩል በተስፋ ከተጣለባቸው የቅን ልቦች ውድድር አሸናፊዎች መካከል ሞያ የ50 ግራም ወርቅ ታላቅ ሽልማት አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ ልጅ ያሬድ የ30 ግራም ወርቅ ሽልማት ተጎናጽፏል። እንዲሁም ጃኒ ስመኝ ግብሩ የ20 ግራም ወርቅ ተሸላሚ በመሆን ስሟን በአሸናፊነት አስመዝግባለች።


















