በቻይና ቤይሀንግ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና ጥናት እና ምርምር እያደርጉ የሚገኙት ኢንጅነር አብዱልከሪም አማን እና ባልደረቦቹ G+1 የመኖሪያ ቤት በ3D ፕሪንተር ማተማቸውን በፌስቡክ ገጻቸው እንደሚከተለው አስፍርዋል።
ለምርምር ቡድኑ YichangDong ከተማ (The City, Where the world largest DAM, Three River Gorge Dam found) በ500 ካሬ መሬት ቦታ ላይ ስፋቱ 100 ካሬ ሜትር ያረፈ G+1 የመኖሪያ ቤት በውስን ቀናት ጋግረን (አትመን) ጨርሰናል።
የሪሰርች ቡድኑ አላማም ይህንን አዲስ የግንባታ ጥበብ ከተለመደው የግንባታ ጥበብ ምን ያክል ተግባራዊ ይሆናል፣ ተቀባይነቱን፣ አዋጭነቱን፣ ምቹ መሆኑን፣ ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆኑን፣ ተፈላጊ የምህንድስና መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን በቤተ ሙከራ እና በተግባር ማረጋገጥ ነው።
የምርምር ቡድኑ Beihang University እና Three gorges Dam University ጋር በመተባበር፤ በአለም ታላቁ ግድብ በሚገኝበት ከተማ YichangDong፤ የ500 ካሬ ሜትር መሬት በማመቻቸት በተግባር G+1 እንድንሰራ የተሰጠንን እድል ተጠቅመን በውስን ቀናቾች ውስጥ ጋግረን(አትመን) ጨርሰነዋል።


እንደሚታዎቀው አብዛሃኞቹ ያደጉም ሆነ ታዳጊ ሃገራት ብሎም በሃገርችን ትልቁ ፈተና የዜጎች የመኖሪያ ቤት እጦት፣ የዋጋ ውድነት እና በበቂ መጠን ማቅረብ አለመቻል ነው። በአሁኑ ሰዓት ዜጎችን እጅጉን እያሳሰበ ያለውን ይህንን የመኖሪያ ቤት እጥረት መፍትሄ ሊኖረው ይችላል ተብሎ የሚገመተው የኮንስትራክሽኑን ኢንዱስትሪ በማዘመን(በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ) እና የግንባታ ጥሬ እቃዎቹን አማራጭ በማብዛት (waste material, plastic,soil…) ነው። በማናቸውም መንግድ የቤት እጦቱ ከህዝብ እድገቱ ጋር ተመጣጥኝ የሚሆንበትን መንገድ መፍትሄ እስካልተገኘ ድረስ ለአሁኑም ሆነ ለመጭው ትውልድ ትልቅ ፈተና ነው።
ይህንን ትኩረት አድርጎ መስራት በቀጣይ ለሪሰርች ቡድኑ ፈታኝ ጉዞ እንደሚያደርገው ይገመታል።
- የትኛውን የግንባታ ጥበብ በቴክኖሎጂ ታግዞ መጠቀም አዋጭ ያደርገዋል? በ3D Concrete Printing ወይስ በተለመደው ?
- ምን አይነትስ ቤቶች ናቸው ለ3D Concrete Printing የአገነባብ ዘዴ በተነጻጻሪ የተሻለ አነስተኛ ዋጋ እና በፍጥነት ማድረስ የሚቻለው?…….ብሎ አዲስ ሞዴል ሃውስ ዲዛይን መፍጠር እና ተግባራዊነቱን Simulate(ስማእል) ማድረግ ግዲ ይላል።
በአሁኑ ወቅት ብዙ ሃገራቶች ቀዳሚ ለመሆን በተግባር እየተጠቀሙበት ሲሆን እንደ Dubai, USA, Austria, China, Germany, Russia, Italy… የመሳሰሉት ሃገሮችን መጥቀስ ቢቻልም፤ ቲክኖሎጅውን ሙሉ በሙሉ ወደ ገበያ አውርዶ ለመተግበር ግን አሁንም ገና ብዙ ጥናት እና ምላሽ የሚፈልጉ ጉዳዮች እንዳሉ ያሳያል።
ቴክኖሎጂው ተቀባይነት የሚኖረው(ወደ ገበያ የሚገባው) እስካሁን ከምንጠቀምባቸው የግንባታ ጥበቦች ያለባቸውን ጉድለቶች ማለትም ተነጻጻሪ የዋጋ ውድነት፣ የግንባታ ጥራት፣ ውበት፣ ጊዜ፣ ከፍተኛ የአካባቢ ብክለትን፣ አማራጭ የግንባታ ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የመሳሰሉት ጉዳዮች መፍታት ሲቻል ብቻ ነው።
ምንጭ፡ Abdulkerim Aman


















