የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው በመቆጠብ ላይ ካሉ ቤት ፈላጊዎች ውስጥ በማህበር ተደራጅተው በጋራ ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸው ተመዝጋቢዎች በማህበር አደረጃጀት መሬት በማስረከብ በተለያዩ ሳይቶች ግንባታ እንዲጀምሩ ማድረጉ ይታወሳል።
በመሆኑም ከማህበር ውስጥ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓደሉ ቢሮው ተጠባባቂዎችን በመዝገብ በማዘጋጀት በሚጓደሉ አባላት ቦታ ተተኪ አባላትን ይመድባል።
በዚህም መሰረት በተጠባባቂነት በመመዝገብ በማህበር ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላችሁ የ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ብቻ በተዘጋጀው ሊንክ በመጠቀም ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

ለዚህ ምዝገባ መሟላት የሚገባቸው መሰረታዊ መስፈርቶች ሲኖሩ እነሱም አመልካቾች የ2005 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች የሆኑ እና እየቆጠቡ የሚገኙ መሆን ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪም ለቤት ግንባታ የሚውለውን 70 በመቶ ገንዘብ ማህበሩ እያስገነባ በሚገኝበት ዋጋ መሰረት ማዋጣት የሚችሉ እና ቀረውን 30 በመቶ ቢሮው ባመቻቸው መሰረት ከባንክ ለመበደር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ምዝገባው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ብቻ የሚካሄድ በመሆኑ ማህበሩን ለማነጋገር ወይም ለአመልካቾች ቢሮ በአካል መምጣት የማያስፈልግ ሲሆን ፍላጎት ያላቸው ተመዝጋቢዎች የሞባይል ስልክዎቻቸውን በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።
ለመመዝገብ የሚፈልጉ አካላት https://forms.gle/3y6E2EmAZSbboRg8A የሚለውን ኦንላይን ሊንክ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እና ዝርዝር ሁኔታዎችን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ማግኘት ይቻላል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

















