ባማኮን ሪል እስቴት መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ደማቅ መርሃ ግብር ተዋናይትና ሞዴል እንዲሁም ጋዜጠኛ ሉላ ገዙን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን በይፋ አስታወቀ።
ሉላ በቀጣይ የድርጅቱን ብራንድ እና እሴቶች በመወከል ከባማኮን ጋር የተለያዩ ስራዎችን ታከናውናለች።
“እንደራሴ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ባማኮን በሪል እስቴት ዘርፍ እያራመደ ካለው የብራንድ ጉዞ ጋር የተያያዘ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።
በዚህ ዝግጅት ላይ በርካታ የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች (influencers) እና አርቲስቶች የተገኙ ሲሆን፣ የባማኮን ሪል እስቴት መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ስለ ድርጅቱ እንቅስቃሴ ገለፃ አድርገዋል።
ባማኮን ሪል እስቴት ወደ ሪል እስቴት ልማት ከመምጣቱ በፊት ከ20 ዓመታት በላይ በግንባታ ዘርፍ ሲሰራ የቆየ ድርጅት ነው። በዚህ ወቅትም በአዲስ አበባ ትላልቅና ውስብስብ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ልምድ ማካበቱን ተገልጿል።
ድርጅቱ አሁን ያካበተውን የግንባታ እውቀትና ተሞክሮ በሪል እስቴት ልማት ላይ በመጠቀም ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸው ፕሮጀክቶችን እያስገነባ ይገኛል።
የባማኮን ሪል እስቴት መስራችና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ግርማ ገላው እንደገለጹት፣ የድርጅቱ ትኩረት ቤት መገንባት ብቻ ሳይሆን ሰዎች የሚኖሩበት፣ የሚያድጉበትና ህይወታቸውን የሚገነቡበትን ስፍራ መፍጠር ነው።
ኢንጂነሩ አክለውም ባማኮን ከግንባታ ዘርፍ ያገኘውን የረጅም ጊዜ ልምድ በሪል እስቴት ልማቱ በመጠቀም ለነዋሪዎች ከቤት ባለፈ የተሟላ የኑሮ ልምድ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በበርካታ የሚዲያ እና የብራንድ ተሳትፎዎች የምትታወቀው ሉላ ገዙ በበኩሏ ከባማኮን ሪል እስቴት ጋር በመተባበር የድርጅቱን የቤት እና የኑሮ እሳቤ ለተለያዩ ደንበኞቹ በማድረስ ላይ ትሳተፋለች።
የባማኮን ሪል እስቴት እንደገለጸው፣ ከሉላ ገዙ ጋር የተጀመረው ስምምነት የድርጅቱን ብራንድ ከህብረተሰቡ ጋር ይበልጥ ለማገናኘትና የሚያቀርባቸውን የሪል እስቴት ፕሮጀክቶች ለሰፊ ተጠቃሚ ለማስተዋወቅ ያግዛል ተብሏል።
በ2018 መጀመሪያ አካባቢ የጋላክሲ ፊኒስሺንግ ሞል በተመረቀበት ወቅት ይፋ ተደርጎ የነበረው የቲክቶክ የይዘት ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች በእለቱ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። በዚህም መሰረት፡
1ኛ የወጣው አሸናፊ፡ 1 ሚሊዮን ብር
2ኛ የወጣው አሸናፊ፡ 250 ሺህ ብር
3ኛ የወጣው አሸናፊ፡ 150 ሺህ ብር ሽልማታቸውን ተረክበዋል።
ከባማኮን ግሩፕ ውስጥ አንዱ የሆነው ባማኮን ሪል እስቴት በተለያዩ ቦታዎች ቅንጡ አፓርትመንቶችን በመገንባት እየሸጠ የሚገኝ ሲሆን በእለቱም አዲሱን ሳይታቸውን በይፋ ስራ አስጀምረዋል።

















